Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 27:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ዳዊት በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፤ “አንድ ቀን ሳኦል እኔን ይገድለኛል፤ እንግዲህ ለእኔ የሚበጀኝ ነገር አምልጬ ወደ ፍልስጥኤም መሄድ ነው፤ ከዚያም በኋላ ሳኦል በእስራኤል ምድር እኔን መፈለጉን ስለሚተው ከእጁ አመልጣለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዳዊት ግን በልቡ፣ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፣ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ ዐሰበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ዳዊት በልቡ፦ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፥ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ አሰበ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዳዊትም በልቡ፦ አንድ ቀን በሳኦል እጅ እጠፋለሁ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሽ በቀር የሚሻለኝ የለም፥ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፥ እንዲህም ከእጁ እድናለሁ አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 27:1
29 Referencias Cruzadas  

በሐሳቡም “ይህ ሁሉ ነገር እንዲህ ሆኖ ሳለ፥ የእኔ ሕዝብ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ በቤተ መቅደሱ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ማቅረባቸው የሚቀጥል ከሆነ፥ ለይሁዳ ንጉሥ ለሮብዓም ታማኞች በመሆን ወደ እርሱ ዞረው እኔን ይገድሉኛል፤ መንግሥቱም ወደ ዳዊት ቤት ይመለሳል” አለ።


በዚህም ጉዳይ ከመከረበት በኋላ የሁለት ጥጆችን ምስል ከወርቅ አሠርቶ ለሕዝቡ “ከዚህ በፊት ታደርጉት በነበረው ዐይነት ለመስገድ እስከ ኢየሩሳሌም መሄድ ይበቃችኋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነሆ እነዚህ ናቸው!” አለ።


ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ። አገልጋዩንም በዚያ ተወው፤


ከዚህ በኋላ ንጉሥ አሜስያስና አማካሪዎቹ በእስራኤል ላይ አሤሩ፤ አሜስያስም የኢዩ የልጅ ልጅ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ እስራኤል ንጉሥ ዮአስ መልእክተኞች በመላክ “እንግዲህ፥ ና ይዋጣልን?” ሲል ለጦርነት አነሣሣው፤


በፍርሃቴ ጊዜ እንኳ “ማንም የሚታመን የለም” አልኩ።


ወደ ሩቅ ስፍራ ተጒዤ መኖሪያዬን በበረሓ ባደረግሁ ነበር።


ይህ ሁሉ እንደሚሆን ገና ከዚያ ሳንወጣ ነግረንህ አልነበረምን? እንዲያውም ‘እባክህ ተወን፥ ለግብጻውያን ባርያዎች ሆነን እናገልግል’ ብለንህ ነበር፤ በእርግጥም በዚህ በረሓ ከመሞት፥ በዚያ ባርያዎች ሆነን መኖር በተሻለን ነበር።”


ተስፋ ሲዘገይ ልብን ያሳዝናል፤ የተመኙት ነገር ሲፈጸም ግን ደስ ያሰኛል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ፤ ታዲያ እንደ ሣር የሚጠወልገውንና መሞት ያለበትን ሰውን የምትፈሩት ለምንድን ነው?


እግዚአብሔር ወደዚያች ምድር የሚወስደን ለምንድን ነው? እኛ ሁላችን በጦርነት እናልቃለን፤ ሚስቶቻችንና ልጆቻችንም ይማረካሉ፤ ወደ ግብጽ ብንመለስ መልካም አይሆንምን?”


ኢየሱስ ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ “አንተ እምነት የጐደለህ! ስለምን ተጠራጠርክ?” አለው።


ኢየሱስም፦ “እንዲህ የምትፈሩት ለምንድን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም?” አላቸው።


መቄዶንያ በደረስን ጊዜ እንኳ ከብዙ አቅጣጫ ችግር ደረሰብን እንጂ ምንም ዕረፍት አላገኘንም፤ በውጭ ጠብ በውስጥም ፍርሀት ነበረብን።


እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ከንጉሥነት ስለ ሻርኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ድረስ ነው? እኔ እርሱ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ ይኖር ዘንድ አልፈልገውም። ይልቅስ የወይራ ዘይት በቀንድ ሞልተህ በመያዝ በቤተልሔም ወደሚኖረው እሴይ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ዘንድ ሂድ፤ እኔ ከእርሱ ልጆች መካከል አንዱን ንጉሥ እንዲሆን መርጬአለሁ።”


ሳሙኤልም በወይራ ዘይት የተሞላውን ቀንድ ወስዶ ዳዊትን በወንድሞቹ ፊት ቀባው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት አደረበት፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ ከእርሱ አልተለየም፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ተመለሰ።


ዳዊት ግን “አባትህ አንተ እኔን ምን ያኽል እንደምትወደኝ በደንብ ያውቃል፤ ስለዚህም ዕቅዱን አንተ እንድታውቅበት ላለማድረግ ወስኖአል፤ ይህንንም የሚያደርገው አንተ ይህን ብታውቅ በብርቱ እንደምታዝን ስለሚያውቅ ነው፤ በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከአሁን ወዲያ ወደ ሞት ለመድረስ የቀረችን አንዲት ዕርምጃ ብቻ ናት!” አለው።


ከዚህ በኋላ ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ “በዚህ አትቈይ፤ አሁኑኑ ፈጥነህ ወደ ይሁዳ ሂድ” ሲል ነገረው፤ ስለዚህም ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።


“አይዞህ አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል በአንተ ላይ ጒዳት ማድረስ ከቶ አይችልም፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና እኔም ከአንተ የምቀጥል ሁለተኛ ማዕርግ እንደሚኖረኝ አባቴ በደንብ ያውቃል።”


እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት፥ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ባደረገልህና በእስራኤልም ላይ በሚያነግሥህ ጊዜ፥


ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ።


አምስቱም የፍልስጥኤም ነገሥታት በመቶና በሺህ ከተመደቡ ሰልፈኞቻቸው ጋር ዘመቱ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም የአኪሽ ደጀን ጦር ሆነው ዘመቱ፤


የፍልስጥኤም ጦር አዛዦችም እነርሱን ባዩ ጊዜ “እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?” ሲሉ ጠየቁ። አኪሽም “ይህማ የእስራኤል ንጉሥ ባለሟል የነበረው ዳዊት አይደለምን? እነሆ እርሱ ከእኔ ጋር ሲኖር ብዙ ጊዜው ነው፤ ሳኦልን ከድቶ ወደ እኔ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ሊያሳዝነኝ የሚችል ምንም ዐይነት በደል ሠርቶ አልተገኘም” ሲል መለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos