ሰቈቃወ 1:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፥ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከከፍታ ስፍራ እሳትን ላከ፤ ወደ ታች ወደ ዐጥንቶቼም ሰደደው፤ በእግሮቼ ላይ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም ጣለኝ፤ ቀኑን ሙሉ በማድከም፣ ባዶ አድርጎ አስቀመጠኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከላይ እሳት ላከ፤ እሳቱም ወደ አጥንታችን ዘለቀ፤ ለእግራችን መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰን፤ ሕሊናችንን አስቶ ቀኑን ሙሉ ሰውነታችን እንዲዝል አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሜም። ከላይ እሳትን ሰደደ፤ አጥንቶችንም አቃጠለ፤ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም፤ ቀኑንም ሁሉ መከራ አጸናብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፥ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ። |
መረቤን በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ፥ በዚያም በእኔ ላይ ለፈጸመው ክሕደት ከእርሱ ጋር እፋረዳለሁ።
እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።
በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። በዚያም ጌታ የሚርድ ልብ፥ ፈዛዛ ዐይኖች፥ ደካማም ነፍስ ይሰጥሃል።