Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሰቈቃወ 1:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና። ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኃጢአቴ ሁሉ እንዳደረግህብኝ አድርግባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ ከኀጢአቴ ሁሉ የተነሣ፣ በእኔ ላይ እንዳደረግህብኝ፣ በእነርሱም ላይ አድርግባቸው፤ የሥቃይ ልቅሶዬ በዝቷል፤ ልቤም ደክሟል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “ ክፉ ሥራቸውን ሁሉ ተመልከት፤ በበደሎቼ ሁሉ ምክንያት በእኔ ላይ እንዳደረግኸው በእነርሱም ላይ አድርግ ዘወትር ስለምቃትት ልቤ እየደከመብኝ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ታው። ልቅ​ሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክ​ሞ​አ​ልና፥ ክፋ​ታ​ቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድ​ረስ፥ ስለ ኀጢ​አቴ ሁሉ እኔን እንደ ቃረ​ም​ኸኝ እነ​ር​ሱን ቃር​ማ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና። ክፋታቸው ሁሉ ወደ ፊትህ ይድረስ፥ ስለ ኃጢአቴ ሁሉ እንዳደረግህብኝ አድርግባቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 1:22
16 Referencias Cruzadas  

ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል።


በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።


ስለዚህ፥ ክብራችሁ ነውና፥ ስለ እናንተ ስለምቀበለው መከራዬ እንዳትታክቱ እለምናችኋለሁ።


በእርጥብ እንጨት ላይ እንዲህ የሚያደርጉ ከሆኑ፥ በደረቀውስ ላይ እንዴት ይሆን?”


ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፥ ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዝዞአል፥


ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፥ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ።


በጽዮን የሚኖሩ እንዲህ ይበሉ፦ “በእኔና በሥጋ ዘመዶቼ ላይ የተደረገ ግፍ በባቢሎን ላይ ይሁን” ኢየሩሳሌምም እንዲህ ትበል፦ “ደሜ በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ ይሁን”።


አንተ ግን፥ አቤቱ! እኔን ለመግደል በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውን ይቅር አትበል፥ ኃጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፥ በቁጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።


ያዕቆብን በልተውታልና፥ ውጠውታልምና፥ አጥፍተውታልምና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አውርድ።


ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።


አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥ ፊትህን ከኔ አትሰውር፥ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን።


አሕዛብ፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ለምን ይበሉ፥ የፈሰሰውን የባርያዎችህን ደም በቀል በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ።


ስለዚህ የሚውጡህ ሁሉ ይዋጣሉ፥ ጠላቶችህም ሁሉ አንድም ሳይቀሩ ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፥ የበዘበዙህንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios