ኢዮብ 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፥ አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ጊዜ በሰላም በተኛሁ፣ አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን በሰላም በተጋደምኩ፥ አንቀላፍቼም ዕረፍት ባገኘሁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፤ አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፥ አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፥ |
እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።”
ከወደቁ ኃያላን ካልተገረዙ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው፥ ሰይፋቸውንም ከራስጌያቸው በታች አድርግው ወደ ሲኦል ከወረዱ ጋር አልተኙም፥ በሕያዋንም ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ኃጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ነበር