Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ኢዮብ 10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “ሕይወቴ ሰለቸኝ፥ የኀዘን እንጉርጉሮዬን እለቅቀዋለሁ፥ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።

2 እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደሆነ ንገረኝ።

3 ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ የክፉዎችንስ ምክር ልታበራ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?

4 በውኑ የሥጋ ዐይን አለህን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን?

5 ቀኖችህ እንደ ሰው ቀኖች ናቸውን? ወይስ ዓመታትህ እንደ ሰው ቀናት ናቸውን?

6 ታዲያ ክፋቴን የምትከታተለው፥ ኃጢአቴንም የምትመረምረው ለምንድን ነው?

7 ከዚህም በላይ በደለኛ እንዳልሆንሁ፥ ከእጅህም የሚያድን እንደሌለ አንተ ታውቃለህ።

8 እጆችህ ቀረጹኝ ሠሩኝም፥ ከዚያም ተመልሰህ ታጠፋኝ ዘንድ ፈለግህ።

9 ከጭቃ እንደሠራኸኝ አስታውስ፥ ወደ ትቢያም ትመልሰኛለህን?

10 በውኑ እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን? እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?

11 ቁርበትና ሥጋ አለበስኸኝ፥ በአጥንትና በጅማትም አጠንከርኸኝ።

12 ሕይወትና ቸርነት አደረግህልኝ፥ መጐብኘትህም መንፈሴን ጠበቀች።

13 እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥ ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ።

14 ኃጢአት ብሠራ አንተ ትመለከተኛለህ፥ ከኃጢአቴም ንጹሕ አታደርገኝም።

15 በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፥ ጻድቅም ብሆን ራሴን አላነሣም፥ ጉስቁልናን ተሞልቻለሁና፥ መከራዬንም ተመልክቻለሁና።

16 ራሴም ከፍ ከፍ ቢል እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፥ ተመልሰህም ድንቅ ነገር ታድርግብኛለህ።

17 ምስክሮችህን ታድስብኛለህ፥ ቁጣህንም ታበዛብኛለህ፥ ጭፍራ በጭፍራ ላይ ትጨምርብኛለህ።”

18 “ስለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዐይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ።

19 እንዳልነበረ በሆንሁ፥ ከማኅፀንም ወደ መቃብር በወሰዱኝ።

20 የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?

21 ወደማልመለስበት ስፍራ ሳልሄድ፥ ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ ምድር፥

22 እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos