ሆሴዕ 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኔ ሸሽተው ሄደዋልና ወዮላቸው! በእኔም ላይ ዐምፀዋልና ጥፋት ይምጣባቸው! እኔ እታደጋቸው ነበር፥ እነርሱ ግን ሐሰትን ተናገሩብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዮ ለእነርሱ፤ ከእኔ ርቀው ሄደዋልና! ጥፋት ይምጣባቸው! በእኔ ላይ ዐምፀዋልና። ልታደጋቸው ፈለግሁ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእኔ ርቀው ስለ ሄዱ ወዮላቸው! በእኔም ላይ ስለ ዐመፁ ጥፋት ይምጣባቸው፤ እኔ ልታደጋቸው ፈልጌ ነበር፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኔ ፈቀቅ ብለዋልና ወዮላቸው! እኔንም ስለ በደሉ ደንግጠዋል! እኔ ታደግኋቸው፤ እነርሱ ግን በሐሰት ተናገሩብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ፈቀቅ ብለዋልና ወዮላቸው! በእኔም ላይ ዐምፀዋልና ጥፋት ይምጣባቸው! እኔ ልታደጋቸው ወደድሁ፥ እነርሱ ግን በሐሰት ተናገሩብኝ። |
ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል ጌታ፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ለመጨመር ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።
ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ ጌታንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
ጌታ ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “በእውነት መቅበዝበዝን ወድደዋል፥ እግራቸውንም አልከለከሉም፤ ስለዚህ ጌታ በእነርሱ ደስ አይሰኝም፥ በደላቸውንም አሁን ያስታውሳል ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።”
እናንተ፦ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ ጌታ ጸልይ፥ ጌታ አምላካችንም የሚናገረውን ሁሉ ንገረን እኛም እናደርገዋለን ብላችሁ ወደ ጌታ ወደ አምላካችሁ እናንተው ልካችሁኝ ነበርና ራሳችሁን አታልላችኋል።
ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፥ እርሷ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሏልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ።
እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፥ በውኑ መንገዴ ቀና አይደለምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?
በሐሰት አድርገዋልና፥ ሌባም ገብቶአልና፥ በገላጣም ስፍራ ወንበዴ ቀምቶአልና፤ እስራኤልን በፈወስሁ ጊዜ የኤፍሬም ኃጢአትና የሰማርያ ክፋት ተገለጠ።
ዮናስ ግን ከጌታ ፊት ወደ ተርሴስ ለመሸሽ ተነሣ፤ ወደ ያፎም ወረደ፥ ወደ ተርሴስም የምትሄድ መርከብ አገኘ፤ ከጌታ ፊት ሸሽቶ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ለመሄድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርሷ ገባ።
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትንም የምትወግሪ፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ልሰበስብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።
አየሁም፤ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት መለከትን በሚነፋበት ጊዜ ከሚቀረው ድምፅ የተነሣ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!”