Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 18:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አባቶች ጎምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች አጠረሰ፥ ብላችሁ ስለ እስራኤል ምድር የምትመስሉት ምሳሌ ምንድነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ስለ እስራኤል ምድር፣ “ ‘አባቶች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤ የልጆችንም ጥርስ አጠረሰ’ እያላችሁ የምትመስሉት ተምሳሌት ምን ለማለት ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “በእስራኤል ምድር ተደጋግሞ የሚነገር ይህ ምሳሌ ምንድን ነው? ‘ወላጆች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤ ነገር ግን የልጆቻቸውን ጥርስ አጠረሰ’ ይላሉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፦ ‘አባ​ቶች ጨርቋ የወ​ይን ፍሬ በሉ፥ የል​ጆ​ችም ጥር​ሶች ጠረሱ’ ብላ​ችሁ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የም​ት​መ​ስ​ሉት ምሳሌ ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ስለ እስራኤል ምድር፦ አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ ብላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድር ነው?

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 18:2
21 Referencias Cruzadas  

አባቶቻችን ኃጢአትን ሠሩ ዛሬም የሉም፥ እኛም በደላቸውን ተሸከምን።


እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅና በተባባሪዎቹ በእስራኤል ነገዶች ያለውን የዮሴፍን በትር እወስዳለሁ፥ ከይሁዳ በትር ጋር አስቀምጣቸዋለሁ፥ አንድ በትር አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም አንድ ይሆናሉ።


ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት፥ አባቶቻችሁም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱ፥ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘለዓለም በእርሷ ይኖራሉ፤ አገልጋዬ ዳዊት ለዘለዓለም ልዑላቸው ይሆናል።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።


ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው።


ሕዝቤን በችግር ስታደቁት፤ የድኾችንም ፊት በኀዘን ስታገረጡት ምን ማለታችሁ ነው?” ይላል ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?


እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።


ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፦ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት ተማርከው በተወሰዱ ጊዜ እሰይ ብለሻልና፤


የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ፥ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ፍጻሜ! በአራቱም የምድሪቱ ማዕዘናት ላይ ፍጻሜ መጥቷል።


እናንተ፦ “እግዚአብሔር በደላቸውን ለልጆቻቸው ይጠብቃል” ብላችኋል። ይልቁንም እራሳቸው ይረዱት ዘንድ ፍዳን ይክፈላቸው።


የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር፦ “ቀኖቹ ረዝመዋል፥ ራእይም ሁሉ ጠፍቶአል” የምትሉት ይህ ምሳሌ ምንድነው?


እነሆ በምሳሌ የሚናገር ሁሉ፦ “ሴት ልጇ እንደ እናቷ ናት” እያለ ምሳሌ ይመስልብሻል።


የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


እኔ ሕያው ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እንግዲህ ወዲህ ይህ ምሳሌ በእስራኤል ውስጥ በእናንተ አይመሰልም።


እናንተ ግን፦ የአባትን ኃጢአት ልጁ ለምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍትሕንና ጽድቅን ቢያደርግ፥ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅና ቢያደርገው በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።


አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios