Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 9:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እርሱን አልሰሙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል፤ በአሕዛብም መካከል ተቅበዝባዦች ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ባለመታዘዛቸው ምክንያት፣ አምላኬ ይጥላቸዋል፤ በአሕዛብም መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እርሱን ስላልታዘዙ አምላኬ ይጥላቸዋል፤ እነርሱም በአሕዛብ መካከል በመንከራተት ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አል​ሰ​ሙ​ት​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ተቅ​በ​ዝ​ባ​ዦች ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አልሰሙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል፥ በአሕዛብም መካከል ተቅበዝባዦች ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 9:17
34 Referencias Cruzadas  

ከእኔ ሸሽተው ሄደዋልና ወዮላቸው! በእኔም ላይ ዐምፀዋልና ጥፋት ይምጣባቸው! እኔ እታደጋቸው ነበር፥ እነርሱ ግን ሐሰትን ተናገሩብኝ።


ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች፤’ አለ።


የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤’” እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም፤ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል ጌታ።


እኔ ግን ወደ ጌታ እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴን አምላክ እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ይሰማኛል።


ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤


“እነሆ፥ አዝዛለሁ፥ እህልም በወንፊት እንደሚነፋ የእስራኤልን ቤት በአሕዛብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።


እነርሱም ይበላሉ አይጠግቡም፥ ያመነዝራሉ አይበዙም ምክንያቱም ጌታን ትተው


ኢሳይያስም እንዲህ አለ፤ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፤ ስሙ፤ የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላኬን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁን?


ብዙ ጊዜ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል፥ ፈውስም የለውም።


የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና፥ በዙሪያው ፍርሃት ነበረ፥ በላዬ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ ነፍሴን ለመንጠቅ ተማከሩ።


አምላኬ ሆይ፥ ለዚህ ሕዝብ ያድረግሁትን ሁሉ ለመልካምነት አስብልኝ።


እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


ሚክያስም፦ “በሕያው ጌታ እምላለሁ! አምላኬ የሚለውን እርሱን እናገራለሁ” አለ።


ፈጽሜ እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ፤’ አልኩ።


የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ያዕቆብ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።


አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ያሟላላችኋል።


ቶማስም “ጌታዬና አምላኬ!” ብሎ መለሰለት።


ኢየሱስም “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ፤’ ብለሽ ንገሪአቸው፤” አላት።


አይሁድም እንዲህ ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ “እኛ እንዳናገኘው ይህ ሰው ወዴት ሊሄድ ነው? በግሪክ ሰዎች መካከል ተበትነው ወደሚኖሩት ሄዶ የግሪክን ሰዎች ሊያስተምር ነውን?


እርሱም፦ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “የበጋ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት ነው” አልኩት። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቷል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ዳግመኛ አላልፋቸውም።


ጌታ ጥሎአቸዋልና ‘የተጣለ ብር’ ብለው ይጠሩአቸዋል።”


“ልጆችን የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ብዙ ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ ማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል አድርጋችሁ ከረከሳችሁ፥ ታስቆጡትም ዘንድ በጌታ በአምላካችሁ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ከሠራችሁ፥


ጌታም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ ጌታ በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ።


አሁንም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስላደረጋችሁ፥ ይላል ጌታ፥ በማለዳም ተነሥቼ ባለማቋረጥ በተናገርኋችሁ ጊዜ ስላልሰማችሁ፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ስላልመለሳችሁ፥


የኤፍሬምንም ዘር ሁሉ፥ ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፥ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ።


ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios