Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 18:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፥ በውኑ መንገዴ ቀና አይደለምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “እናንተ ግን፣ ‘የጌታ መንገድ ቀና አይደለችም’ ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስማ፤ መንገዴ ቀና አይደለችምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “እናንተም ‘እንዲህ ከሆነ እግዚአብሔር የሚያደርገው ነገር ትክክል አይደለም’ ትሉ ይሆናል፤ እናንተ እስራኤላውያን እኔን አድምጡ፤ እኔ የማደርገው ነገር ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ ታስባላችሁን? ነገር ግን ትክክል ያልሆነው የእናንተ አካሄድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “እና​ንተ ግን፦ የጌታ መን​ገድ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ችም ትላ​ላ​ችሁ። የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ መን​ገዴ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ይል​ቅስ የእ​ና​ንተ መን​ገድ ያል​ቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ እንግዲህ ስሙ፥ በውኑ መንገዴ የቀናች አይደለችምን? ይልቅስ የእናንተ መንገድ ያልቀናች አይደለችምን?

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 18:25
29 Referencias Cruzadas  

ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”


ቁጣህን በእግዚአብሔር ላይ እስከ ማንሣት ደርሰህ፥ እነኚህንም ቃላት ከአፍህ እስከ ማውጣት ደርሰህ።


ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቁጣ ነደደ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።


“ይህ ትክክል ነው ብለህ ታስባለህን? ወይስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን?


በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ላይ ትፈርዳለህን?


ጌታ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።


ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ፥ እኔ እንደ አንተ የምሆን መሰለህ፥ እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ።


ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።


የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፥ ልቡም በጌታ ላይ ይቈጣል።


አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?


ጻድቁ ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ በዚያ ቢሞት፥ እርሱ በሠራው በደል ይሞታል።


ሆኖም የእስራኤል ቤት የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ይላሉ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በውኑ መንገዶቼ ቀና አይደሉምን? ቀና ያልሆኑትስ የእናንተ መንገዶች አይደሉምን?


የሕዝብህም ልጆች፦ የጌታ መንገድ የቀና አይደለም ይላሉ፤ ነገር ግን የእነርሱ መንገድ የቀና አይደለም።


እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ የቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በእያንዳንዳችሁ ላይ እንደ መንገዳችሁ እፈርድባችኋለሁ።


በውስጧ ያለው ጌታ ጻድቅ ነው፥ ስሕተት አያደርግም፥ ማለዳ ማለዳ ፍርዱን ለብርሃን ይሰጣል፥ አያቋርጥምም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።


በቃላችሁ ጌታን አሰልችታችሁታል። እናንተም፦ እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው? ትላላችሁ። “ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ፊት መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” በማለታችሁ ነው።


የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባለማወቅ፥ የራሳቸውንም ጽድቅ ለመመሥረት በመፈለግ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።


ምክንያቱም በሕግ ሥራ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና።


ነገር ግን ዐመፃችን የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያጎላ ከሆነ ምን እንላለን? እግዚአብሔር በቁጣ ቢቀጣን ትክክል አይደለም ሊባል ነውን? እንደ ሰው እላለሁ።


ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?


“እርሱ ዐለት፥ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፥ የታመነ አምላክ፥ ተንኮል የሌለበት፥ እርሱ ቀጥተኛና ጻድቅ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos