ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።
ሕዝቅኤል 8:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስድስተኛውም ዓመት፥ በስድስተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያም የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ወደቀች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስድስተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በዐምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፣ በዚያ የጌታ እግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተሰደድን በስድስተኛው ዓመት፥ በስድስተኛው ወር፥ በአምስተኛው ቀን፥ ከይሁዳ የተሰደዱት ሕዝብ መሪዎች በቤቴ ከእኔ ጋር አብረው ተቀምጠው ሳሉ፥ የልዑል እግዚአብሔር ኀይል ድንገት በእኔ ላይ ወረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በስድስተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፥ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስድስተኛውም ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ወደቀች። |
ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።
ስለዚህ ተናገራቸው፥ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማንም ሰው ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊቱ የሚያቆም፥ ወደ ነቢዩም የሚመጣ፥ እኔ ጌታ እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ።
እንዲህም ሆነ በሰባተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ ከወሩም በአሥረኛው ቀን፥ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ሰዎች ጌታን ሊጠይቁ መጡ፥ በፊቴም ተቀመጡ።
ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።
በተሰደድን በሀያ አምስተኛው ዓመት፥ በዓመቱ መጀመሪያ፥ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ በተመታች በዓሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረ፥ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።
ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
እኔም አየሁ፥ እነሆም ሰውን የሚመስል ነበረ፥ ወገቡ ከሚመስለው በታች እሳት፥ ከወገቡም በላይ እንደ ብርሃን የሚመስል፥ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል ነበረ።