ሕዝቅኤል 33:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ሰውየው ከመድረሱ በፊት በነበረው ምሽት፣ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ላይ ነበረች፤ በማለዳም ሰውየው ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ፤ ከዚያ በኋላ ዝም አላልሁም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 አምልጦ የመጣው ሰው እኔ ዘንድ ከመድረሱ ከአንድ ቀን በፊት በምሽቱ የእግዚአብሔር ኀይል ወደ እኔ መጣ፤ በማግስቱ ጠዋት ሰውዬው ወደ እኔ ከመምጣቱ በፊት እግዚአብሔር አንደበቴን ከፈተልኝ፤ ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መናገር አልተሳነኝም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ያመለጠውም ሳይመጣ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተች፤ ከዚያም በኋላ እኔ ዲዳ አልሆንሁም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ያመለጠውም ሳይመጣ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፥ አፌም ተከፈተች ከዚያም በኋላ እኔ ዲዳ አልሆንሁም። Ver Capítulo |