Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 37:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የጌታ እጅ በላዬ ነበረ፥ ጌታም በመንፈሱ አወጣኝ፥ በሸለቆ መካከልም አኖረኝ፤ እሱም አጥንቶች ሞልተውበት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ነበረ፤ እርሱም በእግዚአብሔር መንፈስ አወጣኝ፤ በሸለቆ መካከልም አኖረኝ፤ ሸለቆውም በዐጥንቶች ተሞልቶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የእግዚአብሔር ኀይል በእኔ ላይ መጣ፤ የእርሱም መንፈስ እኔን ወስዶ ብዙ አጥንቶች በተከማቸበት ሸለቆ ውስጥ አኖረኝ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈሱ አወ​ጣኝ፤ አጥ​ን​ቶ​ችም በሞ​ሉ​በት ሸለቆ መካ​ከል አኖ​ረኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ አጥንቶችም በሞሉባት ሸለቆ መካከል አኖረኝ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 37:1
19 Referencias Cruzadas  

እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የጌታ መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ ጌታን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።


“እነሆ! በዚህ ጠንካሮች የሆንን ኀምሳ ሰዎች አለን፤ እንሂድና ጌታህን እንፈልገው፤ ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወስዶ በአንድ ተራራ ላይ ወይም ሸለቆ ውስጥ አሳርፎት ይሆናል።” ኤልሳዕም “አትላኩአቸው” ሲል መለሰ።


ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።


“በጌታ ቤት በር ቁም፥ ይህንም ቃል በዚያ እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ጌታን ልታመልኩ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሆይ! ሁላችሁ የጌታን ቃል ስሙ።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ስፍራ ከመታጣቱ የተነሣ በቶፌት ይቀበራሉና የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ።


በወደዱአቸውና ባገለገሉአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።


የጌታ ቃል፥ በከለዳውያን አገር በኮቦር ወንዝ፥ ወደ ቡዚ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። በዚያም የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ሆነች፥


መንፈስም አነሣኝ፥ በእግዚአብሔርም መንፈስ በራእይ ወደ ከላውዴዎን ወደ ምርኮኞቹ አመጣኝ። ያየሁትም ራእይ ከእኔ ተለየ።


መንፈስ አነሳኝ፥ ወሰደኝም፥ እኔም በምሬትና በመንፈሴ ቁጣ ሄድሁ፥ የጌታም እጅ በላዬ ላይ በርትታ ነበር።


በዚያም የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥ፥ ወደ ሜዳ ውጣ፥ በዚያም ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ።


ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።


በእነርሱ ላይ በዙሪያቸው አሳለፈኝ፤ እነሆ በሸለቆው ፊት እጅግ ብዙ ነበሩ፤ እነሆም፥ በጣም የደረቁ ነበሩ።


በተሰደድን በሀያ አምስተኛው ዓመት፥ በዓመቱ መጀመሪያ፥ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ በተመታች በዓሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረ፥ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።


መንፈስም አነሣኝ፥ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አስገባኝ፤ እነሆ፥ የጌታ ክብር ቤቱን ሞላው።


በስድስተኛውም ዓመት፥ በስድስተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያም የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ወደቀች።


እጅ የሚመስል ዘረጋና በራስ ጠጉሬ ወሰደኝ፥ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፥ በእግዚአብሔርም ራእዮች ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቅናትን የሚያነሣሣ የቅናት ጣዖት ወደሚገኝበት፥ ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው፥ ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ አመጣኝ።


ኢየሱስም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ተመለሰ፤ በምድረ በዳም በመንፈስ ተመራ።


ከውሃውም ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጠቀው፤ ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም፤ ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበርና።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos