የጌታም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር።
ሕዝቅኤል 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ቃል፥ በከለዳውያን አገር በኮቦር ወንዝ፥ ወደ ቡዚ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። በዚያም የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ሆነች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባቢሎናውያን ምድር በኮቦር ወንዝ አጠገብ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቡዝ ልጅ፣ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ በዚያ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የእግዚአብሔር ቃል የቡዚ ልጅ ወደ ሆንኩት ወደ ካህኑ ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቃል በከለዳውያን ሀገር በኮቦር ወንዝ ላይ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወሩም በአምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በከለዳውያን አገር በኮቦር ወንዝ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፥ |
የጌታም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር።
በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በኮቦር ወንዝ በምርኮኞች መካከል ነበርሁ፥ ሰማያት ተከፈቱ፥ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።
በተሰደድን በሀያ አምስተኛው ዓመት፥ በዓመቱ መጀመሪያ፥ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ በተመታች በዓሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረ፥ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።
ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፤ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።
በስድስተኛውም ዓመት፥ በስድስተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያም የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ወደቀች።
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው።
መንፈስ ግን በግልጥ እንዲህ ይላል በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት ትኩረት በመስጠት እምነትን ይክዳሉ፤