Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 8:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በስድስተኛውም ዓመት፥ በስድስተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያም የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ወደቀች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በስድስተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በዐምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፣ በዚያ የጌታ እግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በተሰደድን በስድስተኛው ዓመት፥ በስድስተኛው ወር፥ በአምስተኛው ቀን፥ ከይሁዳ የተሰደዱት ሕዝብ መሪዎች በቤቴ ከእኔ ጋር አብረው ተቀምጠው ሳሉ፥ የልዑል እግዚአብሔር ኀይል ድንገት በእኔ ላይ ወረደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤቴ ተቀ​ምጬ ሳለሁ፥ የይ​ሁ​ዳም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በፊቴ ተቀ​ም​ጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላዬ መጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በስድስተኛውም ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ወደቀች።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 8:1
24 Referencias Cruzadas  

እንዲህም ሆነ በሰባተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር፥ ከወሩም በአሥረኛው ቀን፥ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ሰዎች ጌታን ሊጠይቁ መጡ፥ በፊቴም ተቀመጡ።


ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።


ከእስራኤልም ሽማግሌዎች አንዳንዶች ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ።


ስለዚህ ተናገራቸው፥ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማንም ሰው ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊቱ የሚያቆም፥ ወደ ነቢዩም የሚመጣ፥ እኔ ጌታ እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ።


ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤


የካህን ከንፈሮች ዕውቀትን መጠበቅ አለባቸው፤ ሰዎችም ሕግን ከአፉ መፈለግ አለባቸው፤ ምክንያቱም የሠራዊት ጌታ መልእክተኛ ነው።


በተሰደድን በሀያ አምስተኛው ዓመት፥ በዓመቱ መጀመሪያ፥ ከወሩ በአሥረኛው ቀን፥ ከተማይቱ በተመታች በዓሥራ አራተኛው ዓመት፥ በዚያው ቀን የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረ፥ እርሱም ወደዚያ ወሰደኝ።


የጌታ እጅ በላዬ ነበረ፥ ጌታም በመንፈሱ አወጣኝ፥ በሸለቆ መካከልም አኖረኝ፤ እሱም አጥንቶች ሞልተውበት ነበር።


በዓሥራ ሁለተኛው ዓመት ከወሩም በዓሥራ አምስተኛው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


እንዲህም ሆነ በዓሥራ አንደኛው ዓመት፥ በሦስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


እንዲህም ሆነ በሀያ ሰባተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


በአሥረኛው ዓመት፥ በአሥረኛው ወር ከወሩም በዓሥራ ሁለተኛው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


እንዲህም ሆነ በዓሥራ አንደኛው ዓመት ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


በዘጠነኛው ዓመት፥ በአሥረኛው ወር፥ ከወሩም በአሥረኛው ቀን፥ የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


በዚያም የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥ፥ ወደ ሜዳ ውጣ፥ በዚያም ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ።


መንፈስ አነሳኝ፥ ወሰደኝም፥ እኔም በምሬትና በመንፈሴ ቁጣ ሄድሁ፥ የጌታም እጅ በላዬ ላይ በርትታ ነበር።


መንፈስም አነሣኝ፥ ከኋላዬም የጌታ ክብር ከሥፍራው ይባረክ የሚል ታላቅ የሚያጉረመርም ድምፅ ሰማሁ።


ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።


ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


እኔም አየሁ፥ እነሆም ሰውን የሚመስል ነበረ፥ ወገቡ ከሚመስለው በታች እሳት፥ ከወገቡም በላይ እንደ ብርሃን የሚመስል፥ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል ነበረ።


ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።


እንዲህም ሆነ በዓሥራ አንደኛው ዓመት፥ በመጀመሪያው ወር፥ ከወሩም በሰባተኛው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


እንዲህም ሆነ በዓሥራ ሁለተኛው ዓመት በዓሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios