Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 137 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፥ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።

2 በአኻያ ዛፎች ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።

3 የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም፦ የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።

4 የጌታን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?

5 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ።

6 ባላስታውስሽ፥ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ፥ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።

7 አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።

8 አንቺ ፈራሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።

9 ሕፃኖችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos