እርሱም “በልጁ ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ ምንም ዓይነት ጉዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ለመስጠት እንዳልሳሳህ እነሆ አየሁ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን አውቄአለሁ” አለ።
ዘፀአት 18:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም ከሕዝቡ ሁሉ መስራት የሚችሉ፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ የታመኑ፥ የጉቦ ትርፍን የሚጠሉ ሰዎችን ምረጥ፤ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የዐሥር አለቆችን ሹምላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞችና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ። የሺሕ፣ የመቶ፣ የዐምሳ፣ የዐሥር፣ አለቃ አድርገህ ሹማቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ከሕዝቡ ሁሉ ኀያላን ሰዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን እውነተኞች ሰዎችን፥ ትዕቢትንም የሚጠሉ ሰዎችን ፈልግ። ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የዐሥርም አለቆችን ሹምላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ምረጥ፤ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የአሥርም አለቆችን ሹምላቸው። |
እርሱም “በልጁ ላይ እጅህን አትዘርጋ፤ ምንም ዓይነት ጉዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ለመስጠት እንዳልሳሳህ እነሆ አየሁ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደሆንህ አሁን አውቄአለሁ” አለ።
የግብጽ ምድር በፊትህ ናት፥ በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው፥ በጌሤም ምድር ይኑሩ፤ ከእነርሱ መካከል ችሎታ ያላቸው ሰዎች ካሉ፥ በእኔ እንስሶች ላይ የበላይ ኀላፊዎች አድርገህ ሹማቸው።”
እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የጌታ መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ ጌታን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።
አንተም ዕዝራ፥ በእጅህ እንዳለው እንደ አምላክህ ጥበብ መጠን በወንዝ ማዶ ለሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ የአምላክህን ሕግ በሚያውቁ ሁሉ ላይ እንዲፈርዱ ዳኞችንና ፈራጆችን ሹምላቸው፥ የማያውቁትንም አስተምሩአቸው።
ወንድሜን ሐናኒንና የምሽጉ አዛዥ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ኀላፊነት ሰጠኋቸው፤ እርሱም እውነተኛና ከሌሎች ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
ሙሴም ኢያሱን፦ “ሰዎችን ምረጥልን፥ ከአማሌቅም ጋር ለመዋጋትም ውጣ፤ እኔ ነገ የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ” አለው።
ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ መስራት የሚችሉ ሰዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የዐሥር አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በጭቆና የሚገኝ ትርፍን የሚጸየፍ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚሰበስብ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚከልል፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፥ ተመልከቱም፥ እወቁም፥ በአደባባይዋም ፈልጉ፤ ፍርድን የሚያደርገውን እውነትንም የሚሻውን ሰው ታገኙ እንደሆነ ይቅር እላታለሁ።
ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ወንድሞች ሆይ! በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፤ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤
ከእርሱም ጋር ዐሥር አለቆች ነበሩ፥ ከእስራኤል ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ የአባቶች ቤት አለቃ፤እንያንዳንዱም በእስራኤል አእላፋት መካከል የእየአባቶቻቸው ቤት አለቆች ነበሩ።
አንዳንዶቹን ሻለቆችና አምሳ አለቆች ያደርጋቸዋል፤ ሌሎቹን መሬቱን እንዲያርሱና እህሉን እንዲያጭዱ፥ ሌሎቹን ደግሞ የጦር መሣሪያና ለሠረገላ የሚሆኑትን ዕቃዎች እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።