Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እንዲህም አልኳቸው፦ የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፤ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት መሄድ አይገባችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ስለዚህ በመቀጠል እንዲህ አልሁ፤ “ይህ የምታደርጉት ነገር ትክክል አይደለም፤ የጠላቶቻችንን የአሕዛብን ስድብ ለማስወገድ የአምላካችንን መንገድ በፍርሀት መከተል አይገባችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እኔ ግን ንግግሬን በመቀጠል እንዲህ አልኳቸው፤ “ያደረጋችኹት ነገር ትክክል አይደለም! እግዚአብሔርን መፍራትና ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ በተገባችሁ ነበር፤ ይህን አድርጋችሁ ቢሆን ኖሮ፥ አሕዛብ ጠላቶቻችን ባልተዘባበቱብንም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ደግ​ሞም አልሁ፥ “የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ቡን አም​ላ​ካ​ች​ንን በመ​ፍ​ራት ትሄዱ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ደግሞም አልሁ፦ የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፥ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት ትሄዱ ዘንድ አይገባችሁምን?

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 5:9
21 Referencias Cruzadas  

አብርሃምም አለ፦ “በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንደሌለ፥ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው።


በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ።


ይህን በመፈጸምህ ግን፥ የጌታ ጠላቶች እጅግ እንዲያቃልሉት ስላደረግህ፥ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።”


ይሁዳም፦ “የተሸካሚዎች ኃይል ደክሟል፥ ፍርስራሹም ብዙ ነው፤ ቅጥሩን መሥራት አንችልም” አለ።


እኔ፥ ወንድሞቼና አገልጋዮቼ ገንዘብና እህል አበድረናቸዋል፤ ይህን አራጣ ግን እባካችሁ እንተወው።


ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደውባቸው ነበር፥ ምግብ፥ ወይና አርባ ሰቅል ብር ከእነሱ ይወስዱ ነበር፤ አገልጋዮቻቸው ደግሞ ሕዝቡን ይጨቁኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።


የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል? የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?


ግፈኛ ሰው ወዳጁን ያባብላል፥ መልካምም ወዳይደለ መንገድ ይመራዋል።


ጻድቅን መቅጣት፥ ጨዋ ሰውንም በጻድቅነቱ መምታት መልካም አይደለም።


የጻድቅ ፍርድ ይጠምም ዘንድ፥ ለኀጥእም ማድላት መልካም አይደለም።


ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።


እነዚህ ደግሞ የጠቢባን ቃሎች ናቸው። በፍርድ ላይ ማዳለት መልካም አይደለም።


ወደ ሄዱባቸውም ወደ ሕዝቦች በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነርሱን፦ ከምድሩ የወጡ የጌታ ሕዝብ እነዚህ ናቸው ሲሉአቸው ቅዱስ ስሜን አረከሱ።


ወንድምህ ከአንተ ጋር እንዲኖር ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።


በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።


ይህም “በእናንተ ምክንያት የእግዚአብሔር ስም በሕዝቦች መካከል ይሰደባልና” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።


እንግዲህ ወጣት መበለታት እንዲያገቡ፥ ልጆችንም እንዲወልዱ፥ እያንዳንዳቸውም ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስተዳድሩ እፈቅዳለሁ፤ በዚህም ተቃዋሚ የሚሳደብበትን ምንም ዓይነት ሰበብ እንዳይሰጡት ነው፤


እንዲሁም በእነርሱ አማካይነት የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚቈጣጠሩ፥ ንጹሖች፥ በቤታቸው ውስጥ ሥራቸውን በደንብ የሚያከናውኑ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።


ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር በሚጎበኝበት ቀን፥ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ እርሱን እንድያከብሩት በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።


ልጆቼ ሆይ፥ የጌታን ሕዝብ ኃጢአተኛ በማድረጋችሁ ስለ እናንተ የደረሰኝ ወሬ መልካም አይደለምና ይህ አይሆንም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos