እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች።
ኤርምያስ 12:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወራዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥተዋል፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳ ባሉት ወና ኰረብቶች ላይ፣ አጥፊዎች ይሰማራሉ፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍ፣ አንዳች ሳያስቀር ይበላል፤ የሚተርፍም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድረ በዳ ባሉ በተራቈቱ ኮረብቶች ሁሉ ላይ በዝባዦች መጥተዋል፥ የጌታ ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በረሓማ ከሆነው ከባዶ ተራራ አጥፊዎች ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ሀገሪቱን ከዳር እስከ ዳር ስለሚያጠፋ አንድም ሰው አይድንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወናዎች ኮረብቶች ሁሉ ላይ በዝባዦች መጥተዋል፥ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፥ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም። |
እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች።
እነርሱም፦ ወዴት እንሂድ ቢሉህ፥ አንተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላቸዋለህ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰላሜን፥ ቸርነቴንና ምሕረቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ ታለቅስና ታዝንም ዘንድ አትሂድ።
ዐይኖችሽን አቅንተሽ አንሺ፤ ያልተጋደምሽበት ስፍራ እንዳለም ተመልከች። እንደ ምድረ በዳ ቍራዎች በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ በዝሙትሽና በክፋትሽ ምድሪቱን አርክሰሻታልና።
የእስራኤል ልጆች በመንገዳቸው ዐምጸዋልና፥ ቅዱስ አምላካቸውንም ረስተዋልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእስራኤል ልጆች ልቅሶና ጩኸትም ተሰማ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው ዓመተ ኅድገትን ለማድረግ እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር፥ ለራብም ዓመተ ኅድገትን አውጅባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እበትናችኋለሁ።
ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የአምላካችን የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ በልቶ ይጠግባል፤ በደማቸውም ይሰክራል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መሥዋዕት በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ነውና።
ከእንግዲህ ወዲህ የሞአብ ፈውስ የለም፤ በሐሴቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት” ብለው ክፉ ነገርን አስበውባታል። ፈጽሞ ትተዋለች፤ ከኋላዋ ሰይፍ ይመጣልና።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር ስለ አሞን ልጆችና ስለ ስድባቸው እንዲህ ይላል ብለህ ትንቢት ተናገር፤ ሰይፍ ሰይፍ ለመግደል ተመዝዞአል፤ ጨርሶም ያርድ ዘንድ ተሰንግሎአል በል።
እኔም ጻድቁንና ኃጥኡን ከአንቺ ዘንድ ስለማጠፋ፥ ስለዚህ ሰይፌ ከደቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ በአለ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል።
የእስራትህም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማዪቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጎራዴ ትመታለህ፤ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ፤ እኔም በኋላቸው ጎራዴ እመዝዛለሁ።
እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ በሄዳችሁበትም ሁሉ ሰይፍ ታጠፋችኋለች፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።
በጠላቶቻቸውም ፊት ተማርከው ቢሄዱ በዚያ ሰይፍን አዝዛታለሁ፤ እርስዋም ትገድላቸዋለች፤ ዐይኔንም ለመልካም ሳይሆን ለክፋት በእነርሱ ላይ እጥላለሁ።”
ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፤ ታላቅም ሰይፍ ተሰጠው።