ዳን በጎዳና ላይ እንደሚያደባ እባብ ይሆናል፤ በመንገዱም የፈረሱን ሰኰና እንደሚናደፍ እንደ ቀንዳም እባብ ነው፤ ፈረሰኛውም ወደኋላው ይወድቃል።
ዘፍጥረት 49:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ያድነው ዘንድ ይጠብቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን እጠባበቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላክ ሆይ፥ አዳኝነትህን እጠባበቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚእብሔር ሆይ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ። |
ዳን በጎዳና ላይ እንደሚያደባ እባብ ይሆናል፤ በመንገዱም የፈረሱን ሰኰና እንደሚናደፍ እንደ ቀንዳም እባብ ነው፤ ፈረሰኛውም ወደኋላው ይወድቃል።
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ሥጋዬን ለአንተ እንዴት ልዘርጋልህ
እኔን ለማዳን ረዳትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አምላኬ ነው፤ አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።
በዚያም ቀን፥ “እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፤ ያድናልም፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በመዳናችንም ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን” ይላሉ።
አምላካችን እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፤ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
አሁን እንግዲህ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር ተስማማ፤ የሚቀመጡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶችን እሰጥሃለሁ።
የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ፤ እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር፤ ደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።
በኢየሩሳሌምም ስሙ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ጻድቅና ደግ ሰው ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን ደስታቸውን ያይ ዘንድ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ መንፈስ ቅዱስም ያደረበት ነበር።
እርሱም በአይሁድ በምክራቸውና በሥራቸው አልተባበረም ነበር፤ ሀገሩም የይሁዳ ዕጣ የሚሆን አርማትያስ ነበር፤ እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት ተስፋ ያደርግ ነበር።