ዘፀአት 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እኔን ለማዳን ረዳትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አምላኬ ነው፤ አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 “እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆነልኝ፤ እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ጌታ ኃይሌና መዝሙሬ ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነዋለሁም፥ የአባቴ አምላክ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እግዚአብሔር በመዝሙር የማመሰግነው መከላከያ ኀይሌ ነው፤ ከጠላት እጅ ያዳነኝ ታዳጊዬም እርሱ ነው፤ እርሱ አምላኬ ስለ ሆነ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴም አምላክ ስለ ሆነ፥ ስለ ገናናነቱ እዘምራለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ጉልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፤ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ። Ver Capítulo |