ዘፍጥረት 47:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም በግብፅ ምድር በጌሤም ሀገር ተቀመጠ፤ እርስዋም ርስታቸው ሆነች፤ በዙ፤ እጅግም ተባዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በግብጽ አገር በጌሤም ይኖሩ ነበር፤ በዚያም ሀብት ንብረት ዐፈሩ፤ ቍጥራቸውም እጅግ እየበዛ ይሄድ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም በግብጽ ምድር በጌሤም አገር ተቀመጠ፥ ገዙአትም፥ ረቡ፥ እጅግም በዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በግብጽ አገር ጌሴም በተባለ ምድር ይኖሩ ነበር፤ እዚያም ብዙ ሀብት አገኙ፤ ብዙ ልጆችም ወለዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም በግብፅ ምድር በጌሤም አገር ተቀመጠ ገዙአትም ረቡ እጅግም በዙ። |
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፤ ይህችንም ምድር ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤
ዘርህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እስከ ባሕርና እስከ አዜብ እስከ መስዕና እስከ ምሥራቅ ይበዛል፤ ይሞላልም፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ፥ በዘርህም ይባረካሉ።
እግዚአብሔርም አለው፥ “አምላክህ እኔ ነኝ፤ ብዛ፤ ተባዛም፤ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፤ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ።
አለውም፥ “የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መውረድን አትፍራ፤ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና።
ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ፤ ፈርዖን እንዳዘዘላቸውም በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ርስትን ሰጣቸው።
ከምድርም ላይ ውኃዉ ጐድሎ እንደሆነ ያይ ዘንድ ቁራውን ላከው፤ እርሱም ሄደ፤ ነገር ግን ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ አልተመለሰም።
ነገር ግን ርግብ እግርዋን የምታሳርፍበት ስፍራ አላገኘችም፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ተመለሰች፤ ውኃው በምድር ላይ ሁሉ ነበረና፤ እጁን ዘረጋና ተቀበላት፤ ወደ እርሱም ወደ መርከብ ውስጥ አገባት።
ነገር ግን እንዳስጨነቁአቸው መጠን እንዲሁ በዙ፤ እጅግም ጸኑ ፤ ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች ይጸየፉአቸው ነበር።
አባቶችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁን ግን አምላክህ እግዚአብሔር ብዛትህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አደረገ።
በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ አባቴ ከሶርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም በቍጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ታላቅና የበረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።