የተቀደሰውንም ሰንበትህን አስታወቅሃቸው፤ ትእዛዝንና ሥርዐትን፥ ሕግንም በባሪያህ በሙሴ እጅ አዘዝሃቸው።
ዘፀአት 31:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጃችሁ ምልክት ነውና ሰንበቴን ፈጽሞ ጠብቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤ ‘ሰንበቴን ማክበር አለባችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ምልክት ይሆናል፤ ይኸውም የምቀድሳችሁ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ እንድታውቁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተ ግን ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ፥ ይህ የምቀድሳችሁ ጌታ እኔ እንደሆንሁ እንድታውቁ በእኔና በእናንተ መካከል ለትውልዶቻችሁ ምልክት ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ እግዚአብሔር እናንተን ለእኔ የተለየ ሕዝብ አድርጌ የመረጥኳችሁ መሆኔን የሚያሳይ ሆኖ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በእኔና በእናንተ መካከል ጸንቶ የሚኖር ምልክት ስለ ሆነ የዕረፍት ቀን አድርጌ የመረጥኩትን ሰንበትን ጠብቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጃችሁ ምልክት ነውና ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ። |
የተቀደሰውንም ሰንበትህን አስታወቅሃቸው፤ ትእዛዝንና ሥርዐትን፥ ሕግንም በባሪያህ በሙሴ እጅ አዘዝሃቸው።
እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ሥራውን ፈጽሞ ስላረፈ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘለዓለም ምልክት ነው።”
ይህን የሚያደርግ በእርሱም ጸንቶ የሚኖር፥ ሰንበታትንም የሚጠብቅና የማያረክስ፥ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ሰው ብፁዕ ነው።”
ከቤቶቻችሁ በሰንበት ቀን ሸክምን አታውጡ፤ ሥራንም ሁሉ አትሥሩ፤ አባቶቻችሁንም እንዳዘዝኋቸው የሰንበትን ቀን ቀድሱ።
የምቀድሳቸውም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ምልክት ይሆኑ ዘንድ ሰንበታቴን ሰጠኋቸው።
ሰንበታቴንም ቀድሱ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሁኑ።
መቅደሴም ለዘለዓለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስራኤልን የምቀድሰው እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ።”
ክርክርም በሆነ ጊዜ ለመፍረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍረዱ፤ በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዐቴን ይጠብቁ፤ ሰንበታቴንም ይቀድሱ።
የአምላክህን መባ ያቀርባልና ስለዚህ ትቀድሰዋለህ፤ እኔም የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና እርሱ ቅዱስ ይሁንልህ።
ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው፤ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆንበታል፤ ምንም ሥራ አትሠሩም፤ በምትኖሩበት ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ እኔ የምሰጣችሁ ምድር ታርፋለች፤ ለእግዚአብሔርም ሰንበት ታደርጋለች።
“እህልን እንሸጥ ዘንድ መባቻው መቼ ያልፋል? የኢፍ መስፈሪያውንም እያሳነስን፥ ሰቅሉንም እያበዛን፥ በሐሰተኛም ሚዛን እያታለልን፥
የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።