Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 31:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በስ​ድ​ስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሥራ​ውን ፈጽሞ ስላ​ረፈ፥ በእ​ኔና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የዘ​ለ​ዓ​ለም ምል​ክት ነው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ለዘላለም ምልክት ይሆናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ሠርቶ፣ በሰባተኛው ቀን ከሥራ ታቅቦ ዐርፏልና።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በእኔና በእስራኤል ልጆች መካከል የዘለዓለም ምልክት ነው፤ ጌታ ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ፈጥሮአልና፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው አርፎአልና፥ ተነቃቅቶአልና።’”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እኔ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ ከፈጠርኩ በኋላ ሰባተኛው ቀን ሥራዬን አቁሜ ያረፍኩበት ስለ ሆነ በእኔና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር ምልክት ይሁን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ስላረፈና ስለ ተነፈሰ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘላለም ምልክት ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 31:17
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ጠ​ረ​ውን ሁሉ እጅግ መል​ካም እን​ደ​ሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋ​ትም ሆነ፤ ስድ​ስ​ተ​ኛም ቀን ሆነ።


ከዋ​ክ​ብት በተ​ፈ​ጠሩ ጊዜ መላ​እ​ክቴ ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ አመ​ሰ​ገ​ኑኝ


እርሱ ተና​ገረ፥ የውሻ ዝንብ ትን​ኝም በም​ድ​ራ​ቸው ሁሉ መጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስ​ድ​ስት ቀን ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ ፈጥሮ በሰ​ባ​ተ​ኛዋ ቀን ዐር​ፎ​አ​ልና፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ን​በ​ትን ቀን ባር​ኮ​ታል፤ ቀድ​ሶ​ታ​ልም።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እኔ የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ ዘንድ ለልጅ ልጃ​ችሁ ምል​ክት ነውና ሰን​በ​ቴን ፈጽሞ ጠብቁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ዕረ​ፍት ያደ​ርጉ ዘንድ ሰን​በ​ትን ይጠ​ብቁ።


ፈቃ​ድ​ህን በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀኔ ከማ​ድ​ረግ እግ​ር​ህን ከሰ​ን​በት ብት​መ​ልስ፥ ሰን​በ​ት​ንም ደስታ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ብታ​ደ​ር​ገው፥ ክፉ ሥራን ለመ​ሥ​ራት እግ​ር​ህን ባታ​ነሣ፥ በአ​ፍ​ህም ክፉ ነገ​ርን ባት​ና​ገር፥


ለእ​ነ​ር​ሱም መል​ካ​ምን በማ​ድ​ረግ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም በፍ​ጹም ልቤና በፍ​ጹም ነፍሴ በዚ​ህች ምድር እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ምል​ክት ይሆኑ ዘንድ ሰን​በ​ታ​ቴን ሰጠ​ኋ​ቸው።


ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ቀድሱ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምል​ክት ይሁኑ።


ወደ ዕረ​ፍቱ የገ​ባስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሥ​ራው እንደ ዐረፈ፥ እነሆ፥ እርሱ ከሥ​ራው ሁሉ ዐረፈ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos