መዝሙር 120:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከራ በደረሰብኝ ጊዜ፥ ወደ እግዚአብሔር ጮኽኩ፤ እርሱም ሰማኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዕርገት መዝሙር። በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥ ሰማኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይምጣ? |
እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።
“እግዚአብሔር ሆይ! ተጨንቄ ሳለሁ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ አንተም መለስክልኝ፤ ርዳታህን ለማግኘት ጥልቅ ከሆነው ከሙታን ዓለም ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ሰማኸኝ።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።