ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ዘኍል 12:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ አላቸው፤ “ቃሌን ስሙ፤ “የእግዚአብሔር ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር፣ በራእይ እገለጥለታለሁ፤ በሕልምም እናገረዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለ፦ “እባካችሁ፥ ቃሎቼን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ ጌታ በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ለእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራእይ እገለጥለታለሁ፤ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ። |
ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
አሁን ግን ሴቲቱን ለባልዋ መልሰህ ስጥ፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ እንዳትሞት ይጸልይልሃል፤ እርስዋን መልሰህ ባትሰጥ ግን እንደምትሞት ዕወቅ፤ አንተ ብቻ ሳትሆን ሕዝብህም በሙሉ ታልቃላችሁ።”
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ሌላ ሕልም አይቶ ወንድሞቹን “እነሆ፥ ሌላ ሕልም አየሁ፤ በሕልሜም ፀሐይ፥ ጨረቃና ዐሥራ አንድ ከዋክብት ሰገዱልኝ” አላቸው።
ሰሎሞን ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ ያነጋገረው መሆኑን ተገነዘበ፤ ከዚህ በኋላ ሰሎሞን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆሞ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ከዚህም በኋላ ባለሟሎቹ ለሆኑ ባለሥልጣኖች ሁሉ ግብዣ አደረገ።
አንድ ጊዜ በራእይ ለታማኝ አገልጋይህ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “አንዱን ታላቅ ጀግና ረድቼአለሁ፤ ከሕዝቤ መካከል መርጬ ዘውድን አቀዳጅቼዋለሁ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አደርግሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን እንደ ነቢይ ሆኖ ስለ አንተ ይናገራል፤
ሕልም ያለመ ነቢይ ቢኖር ሕልሙን ብቻ ይናገር፤ ቃሌን የሰማ ነቢይ ግን ያንኑ ቃል በታማኝነት ይናገር፤ ገለባ ከስንዴ ጋር ምን ግንኙነት አለው?
በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፤ ዳንኤል ሕልምና ራእይ አየ፤ ከዚያም በኋላ ያየውን ሕልም ጻፈ።
ይህም ሁሉ ሆኖ በገለዓድ ለጣዖት ይሰግዳሉ፤ ለጣዖት የሚሰግዱት ግን ከንቱ ይሆናሉ፤ በጌልገላ ወይፈኖችን ለመሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ነገር ግን መሠዊያዎቻቸው ተሰባብረው በእርሻ መካከል የድንጋይ ክምር ሆነው ይቀራሉ።”
የእግዚአብሔር መልአክ በቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ አየሁ። እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆመ፤ በስተኋላውም ቀይ፥ ሐመርና አምባላይ ፈረሶች ይከተሉት ነበር።
ነገር ግን ይህን ነገር ሲያስብ ሳለ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “የዳዊት ዘር ዮሴፍ ሆይ! እጮኛህ ማርያም የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ስለ ሆነ፥ እርስዋን ወደ ቤትህ ለመውሰድ አትፍራ።
ስለዚህ እነሆ፥ እኔ ነቢያትን፥ ጥበበኞችን፥ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ አንዳንዶቹንም በምኲራባችሁ ትገርፋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማም ታሳድዱአቸዋላችሁ
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ኢየሩሳሌም፥ ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ! ወደ አንቺ የተላኩትንም በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ፥ እኔም የአንቺን ልጆች በአንድነት ልሰበስብ ስንት ጊዜ ፈቀድኩ! እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።
ከዚህም በላይ ጲላጦስ በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ ሌሊት በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ በንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።
ዘካርያስ ከቤተ መቅደስ በወጣ ጊዜ ከሰዎቹ ጋር መነጋገር አልቻለም፤ ስለዚህ እነርሱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ራእይ የታየው መሆኑን ዐወቁ፤ እርሱ በእጁ እየጠቀሰ ያስረዳቸው ነበር። በዚህም ሁኔታ ዱዳ ሆኖ ቈየ።
ጴጥሮስ የራእዩ ፍች “ምን ይሆን?” እያለ በሐሳቡ ሲጨነቅ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በጥያቄ የስምዖንን ቤት አግኝተው በበር ቆመው ነበር፤
እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ አንዳንዶቹ ነቢያት፥ አንዳንዶቹ የወንጌል ሰባኪዎች፥ አንዳንዶቹ የምእመናን እረኞች፥ አንዳንዶቹ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ስጦታዎችን ሰጣቸው።
እንደ አንተ ያለ ሌላ ነቢይ ከወንድሞቻቸው መካከል አስነሣላቸዋለሁ፤ እርሱ የሚናገረውን ቃል እሰጠዋለሁ፤ እኔም የማዘውን ሁሉ ለሕዝቡ ይነግራል፤
እነዚህ ሁለቱ ነቢያት የምድር ሰዎችን አስጨንቀው ስለ ነበረ በምድር የሚኖሩ ሰዎች በነቢያቱ ሞት ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም በዓል ያደርጋሉ፤ ስጦታም ይለዋወጣሉ።
ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባው እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔር ግን በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አማካይነት መልስ እንዲሰጠው አልፈቀደም።