Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 3:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔርም በሴሎ መገለጡን ቀጠለ፤ እዚያም በቃሉ ለሳሙኤል ተገለጠለት። የሳሙኤልም ቃል በመላው እስራኤል ተደማጭነትን አገኘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ በዚያም እግዚአብሔር ቃል አማካይነት ራሱን ለሳሙኤል ገለጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጌታም በሴሎ ይገለጥ ነበር፤ በዚያም ጌታ በቃሉ አማካይነት ራሱን ለሳሙኤል ገለጠ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ በሴሎ ተገ​ለጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሳ​ሙ​ኤል ይገ​ለ​ጥ​ለት ነበ​ርና። ሳሙ​ኤ​ልም ከም​ድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ እንደ ሆነ ታመነ። ዔሊም እጅግ አረጀ፥ ልጆቹ ግን በክ​ፋት ጸን​ተው ኖሩ፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እግዚአብሔርም ደግሞ በሴሎ ተገለጠ፥ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ቃል ለሳሙኤል በሴሎ ይገለጥ ነበር። የሳሙኤልም ቃል ለእስራኤል ሁሉ ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 3:21
12 Referencias Cruzadas  

ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር።


እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።


ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።


እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም “እነሆ አለሁ ጌታዬ” አለ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤


እግዚአብሔር በቀድሞ ዘመናት በተለያዩ መንገዶች፥ በነቢያት አማካይነት ለአባቶቻችን ብዙ ጊዜ ተናግሮ ነበር፤


ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት አስቀድሞ ሳይገልጥ ምንም ነገር አያደርግም።


እግዚአብሔርም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ከዚያም በፊት ያደርግ በነበረው ዐይነት “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር” አለው።


ከሴኬም፥ ከሴሎና ከሰማርያ ሰማኒያ ሰዎች በድንገት መጡ፤ እነርሱም በሐዘን ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውን ቀደው፥ ፊታቸውን ነጭተው ነበር፤ ለቤተ መቅደስም መባ የሚያቀርቡትን እህልና ዕጣን ይዘው ነበር፤


“እነሆ፥ ዛሬ እናንተ የየነገድ መሪዎቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁ፥ ሹሞቻችሁ፥ ሌሎችም የእስራኤል ወንዶች ሁሉና ልጆቻችሁ፥ ሴቶቻችሁ፥ በእናንተ ሰፈር ሆነው እንጨት የሚለቅሙላችሁና ውሃ የሚቀዱላችሁ መጻተኞች፥ ሁላችሁም በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት ቆማችኋል።


ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል እንዲህ ብሎ ገልጦለት ነበር፤


ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቀታችሁ ያዳናችሁን አምላካችሁን ትታችኋል፤ እናንተም፦ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አላችሁት። ስለዚህ አሁን በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ”።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios