Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 10:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ጴጥሮስ የራእዩ ፍች “ምን ይሆን?” እያለ በሐሳቡ ሲጨነቅ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በጥያቄ የስምዖንን ቤት አግኝተው በበር ቆመው ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ጴጥሮስም ስላየው ራእይ ትርጕም እጅግ ተጨንቆ በማሰላሰል ላይ ሳለ፣ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች የስምዖንን ቤት ፈልገው ካገኙ በኋላ መጥተው በሩ ላይ ቆሙ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጴጥሮስም ስላየው ራእይ “ምን ይሆን?” ብሎ በልቡ ሲያመነታ፥ እነሆ፥ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች ስለ ስምዖን ቤት ጠይቀው ወደ ደጁ ቀረቡ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ጴጥ​ሮ​ስም ስለ አየው ራእይ ምን እንደ ሆነ ሲያ​ወ​ጣና ሲያ​ወ​ርድ ከቆ​ር​ኔ​ሌ​ዎስ ተል​ከው የመጡ ሰዎች የስ​ም​ዖ​ንን ቤት እየ​ጠ​የቁ በደጅ ቁመው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ጴጥሮስም ስላየው ራእይ፦ “ምን ይሆን?” ብሎ በልቡ ሲያመነታ፥ እነሆ፥ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች ስለ ስምዖን ቤት ጠይቀው ወደ ደጁ ቀረቡ፤

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 10:17
9 Referencias Cruzadas  

እግራቸውን ካጠበ በኋላ ልብሱን ለበሰና ወደ ቦታው ተመልሶ ተቀመጠ፤ እንዲህም አላቸው፦ “ምን እንዳደረግሁላችሁ አስተዋላችሁን?


አንድ ቀን በዘጠኝ ሰዓት ገደማ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባና “ቆርኔሌዎስ!” ብሎ ሲጠራው በራእይ በግልጥ ታየው።


ስለዚህ ሁሉም ተገርመውና የሚሉትን አጥተው “ይህ ነገር ምን ይሆን!” ተባባሉ።


እኔም እንዲህ ዐይነቱን ነገር መመርመር ስለ ቸገረኝ ጳውሎስን ‘ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ እዚያ በዚህ ነገር ልትፋረድ ትወዳለህን?’ አልኩት።


የቤተ መቅደሱ የዘብ አዛዥና የካህናት አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ “ይህ ነገር ምን ይሆን?” በማለት ግራ ተጋቡ።


በዚያን ጊዜ በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታ በራእይ “ሐናንያ!” ብሎ ጠራው፤ እርሱም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” አለ።


ጴጥሮስም ስምዖን ከሚባለው አንድ ቊርበት ፋቂ ጋር ለብዙ ቀኖች በኢዮጴ ተቀመጠ።


ከእነርሱ ውስጥ የነበረውም የክርስቶስ መንፈስ በመሲሑ ላይ ስለሚደርሰው መከራና ከመከራውም በኋላ ስለሚያገኘው ክብር አስቀድሞ አመልክቶ ነበር፤ እነርሱም ይህ ሁሉ በምን ጊዜና በእንዴት ያለ ሁኔታ እንደሚሆን መርምረው ነበር፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos