የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ማስታወቂያዎች


ንዑስ ምድብ

104 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ስለ ወርቅ

ወርቅ እሳት ውስጥ ይቀልጣል፤ ንፁህና የጠራ ይሆን ዘንድ። እሳቱ መጠኑን ካለፈ ግን ወርቁ ሊጎዳ ይችላል። ከዚያም በኋላ ወርቁ ይመታል፣ ቅርፁን እስኪያገኝ ድረስ። በእያንዳንዱ ደረጃ ውበቱ እየጨመረ ያበራል፤ ዋጋውም ከፍ ይላል።

በቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ "እርሱ ግን የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝ በኋላ እንደ ወርቅ ንጹሕ ሆኜ እወጣለሁ።" (ኢዮብ 23:10) ለመቀበል አስቸጋሪ ቢሆንም ይህ ምሳሌ ለእኛም ሕይወት ይሠራል። እንዲቃጠሉና የእግዚአብሔር ብርሃን በእኛ ውስጥ እንዲያበራ ልናስተካክላቸው የሚገቡን ባሕሪዎችና ልማዶች አሉን። በትሕትና እንደ ወርቅ ንፁህ ሆነን እንድንወጣ እግዚአብሔር ይፈትነናል።


መዝሙር 119:127

ስለዚህ ከወርቅ፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ፣ ትእዛዞችህን ወደድሁ።

1 ነገሥት 6:32

በሁለቱ የወይራ ዕንጨት መዝጊያዎችም ላይ ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈነዱ አበቦችን ቀረጸ፤ በወርቅም ለበጣቸው።

መዝሙር 19:10

ከወርቅ ይልቅ የከበረ፣ እጅግ ከጠራ ወርቅም የተሻለ ነው፤ ከማር ይልቅ ይጣፍጣል፤ ከማር ወለላም ይበልጥ ይጥማል።

ኢሳይያስ 13:12

ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፣ ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ።

ዘፀአት 25:24

በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።

ዘፍጥረት 2:11-12

የመጀመሪያው፣ ወርቅ በሚገኝበት በኤውላጥ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የፊሶን ወንዝ ነው።

ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፣ መልካም መዐዛ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኙበት ምድር ነው።

ሐጌ 2:8

‘ብሩ የእኔ ነው፤ ወርቁም የእኔ ነው’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤

ዳንኤል 2:32

የምስሉ ራስ ከንጹሕ ወርቅ፣ ደረቱና ክንዶቹ ከብር፣ ሆዱና ጭኖቹ ከናስ የተሠሩ ነበሩ፤

ዘፍጥረት 13:2

አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ እጅግ በልጽጎ ነበር።

ምሳሌ 17:3

ብር በማቅለጫ፣ ወርቅም በከውር፤ እግዚአብሔርም ልብን ይፈትናል።

ዘፍጥረት 24:22

ግመሎቹ ጠጥተው ካበቁ በኋላ ሰውየው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበትና ዐሥር ሰቅል የሚመዝኑ ሁለት የወርቅ አምባሮች አውጥቶ፣

ራእይ 3:18

ስለዚህ ሀብታም እንድትሆን፣ በእሳት የነጠረ ወርቅ እንድትገዛ፣ የዕራቍትነትህ ኀፍረት እንዳይታይ፣ ነጭ ልብስ እንድትለብስና ለማየት እንድትችል ዐይንህን በኵል እንድትኳል እመክርሃለሁ።

ራእይ 21:21

ዐሥራ ሁለቱም በሮች ዐሥራ ሁለት ዕንቍዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱም በር ከአንድ ዕንየተሠራ ነበረ። የከተማዪቱም አውራ መንገድ እንደ መስተዋት ብርሃን የሚያስተላልፍ ንጹሕ ወርቅ ነበረ።

ሰቈቃወ 4:1

ወርቁ እንዴት ደበሰ! ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ! የከበሩ ድንጋዮች፣ በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል።

ዘፍጥረት 24:53

ከዚያም የወርቅና የብር ጌጣጌጥ፣ እንዲሁም ልብሶች አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ደግሞም ለወንድሟና ለእናቷ ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸው ስጦታዎች ሰጣቸው።

ዘፀአት 3:22

እያንዳንዷ ዕብራዊት ከጎረቤቷም ይሁን ዐብራት ከምትኖረው ግብጻዊት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች እንደዚሁም ልብስ እንድትሰጣት ትጠይቅ። እነዚህንም ሁሉ ወስዳችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ታስጌጧቸዋላችሁ፤ ታለብሷቸዋላችሁም። በዚህም መንገድ የግብጻውያኑን ሀብት በእጃችሁ አግብታችሁ ትወጣላችሁ።”

ዘፀአት 11:2

ለእስራኤል ሕዝብ፣ ለወንዶቹም ሆነ ለሴቶቹ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ከየጎረቤቶቻቸው ስጡን ብለው እንዲወስዱ ንገራቸው።”

ዘፀአት 12:35-36

እስራኤላውያን ሙሴ እንዳዘዛቸው የብርና የወርቅ ዕቃዎች፣ እንደዚሁም ልብስ እንዲሰጧቸው ግብጻውያኑን ጠየቋቸው።

እግዚአብሔር በግብጻውያን ፊት ለእስራኤላውያን ሞገስ ስለ ሰጣቸው፣ የጠየቋቸውን ሁሉ ሰጧቸው፤ ስለዚህ የግብጻውያንን ንብረት በዝብዘው ወሰዱ።

ዘፀአት 25:3

“ከእነርሱ የምትቀበላቸው ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፤ “ወርቅ፣ ብርና፣ ንሓስ፤

ዘፀአት 25:11

ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አብጅለት።

ዘፀአት 25:17-18

“ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራለት።

በስርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ የሚሆኑ ከወርቅ የተቀረጹ ሁለት ኪሩቤል ሥራ።

ዘፀአት 28:36

“ከንጹሕ ወርቅ ዝርግ ሳሕን አበጅተህ፣ ቅዱስ ለእግዚአብሔር በማለት በማኅተም ላይ እንደሚቀረጽ ቅረጸው።

ዘፀአት 32:2-4

አሮንም፣ “የሚስቶቻችሁን፣ የወንድና የሴት ልጆቻችሁን የጆሮ ወርቅ አውልቃችሁ ወደ እኔ አምጡ” ብሎ መለሰላቸው።

ያበጁትን ጥጃ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ከዚያም ዱቄት እስኪሆን ፈጨው፤ በውሃ ላይ በተነው፤ እስራኤላውያንም እንዲጠጡት አደረገ።

ሙሴም አሮንን፣ “ወደዚህ አስከፊ ኀጢአት ትመራቸው ዘንድ እነዚህ ሕዝብ ምን አደረጉህ?” አለው።

አሮንም መልሶ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አትቈጣ” ብሎ መለሰለት፤ “ይህ ሕዝብ ሁልጊዜ ለክፋት ያዘነበለ መሆኑን አንተ ታውቃለህ።

እነርሱም ‘በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ያ ከግብጽ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳገኘው አናውቅም’ አሉኝ።

ስለዚህ፣ ‘ማንኛውም ዐይነት የወርቅ ጌጣጌጥ ያለው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው፤ ከዚያም ወርቁን ሰጡኝ፤ ወደ እሳቱ ጣልሁት፤ ይህም ጥጃ ወጣ።”

ሕዝቡ ከቍጥጥር ውጭ እንደ ሆኑ፣ አሮንም መረን እንደ ለቀቃቸውና በጠላቶቻቸውም ዘንድ መሣለቂያ እንደ ሆኑ ሙሴ አስተዋለ።

ስለዚህ በሰፈሩ መግቢያ ላይ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ ሌዋውያኑም ሁሉ ከርሱ ጋራ ሆኑ።

ከዚያም፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘እያንዳንዱ ሰው በወገቡ ላይ ሰይፍ ይታጠቅ፤ በሰፈር ውስጥ ከዳር እዳር እየተመላለሰ እያንዳንዱ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል’ ” አላቸው።

ሌዋውያኑ ሙሴ እንዳዘዛቸው ፈጸሙ፤ በዚያም ዕለት ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ዐለቁ።

ከዚያም ሙሴ፣ “በራሳችሁ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች ላይ በመነሣታችሁ፣ በዛሬዋ ቀን ለእግዚአብሔር የተለያችሁ ሆናችኋል፤ በዛሬዋም ዕለት ባርኳችኋል” አለ።

ሕዝቡም ሁሉ የጆሮ ወርቃቸውን አውልቀው ወደ አሮን አመጡ።

በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን፣ “እጅግ የከፋ ኀጢአት ሠርታችኋል፤ አሁን ግን ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ፤ ምናልባት ኀጢአታችሁን ማስተስረይ እችል ይሆናል” አላቸው።

ስለዚህ ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ እንዲህ አለው፤ “ወዮ እነዚህ ሕዝብ የሠሩት ምን ዐይነት የከፋ ኀጢአት ነው! ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት ሠሩ።

አሁን ግን አቤቱ ኀጢአታቸውን ይቅር በል፤ አለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ እኔን ደምስሰኝ።”

እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ።

አሁን ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ተናገርሁት ስፍራ ምራው፤ መልአኬም በፊትህ ይሄዳል፤ ሆኖም የምቀጣበት ጊዜ ሲደርስ፣ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”

አሮን በሠራው ጥጃ ባደረጉት ነገር እግዚአብሔር ሕዝቡን በመቅሠፍት መታ።

እርሱም የሰጡትን ወስዶ በመሣሪያ በመቅረጽ በጥጃ ምስል ጣዖት አድርጎ ሠራው፤ ከዚያም እነርሱ፣ “እስራኤል ሆይ፤ ከግብጽ ያወጡህ አማልክት እነዚህ ናቸው” አሉ።

ዘፀአት 37:2

በውስጥና በውጭ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።

ዘፀአት 37:6

ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ከንጹሕ ወርቅ የስርየት መክደኛ ሠራ።

ዘፀአት 37:16

የጠረጴዛውን ዕቃዎች ይኸውም ዝርግ ሳሕኖችን፣ ድስቶችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን እንዲሁም የመጠጥ መሥዋዕቱ ማፍሰሻ የሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠሯቸው።

ዘፀአት 37:23-24

የመቅረዙን ሰባት መብራቶች፣ እንዲሁም መኰስተሪያዎችንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩ።

መቅረዙንና ዕቃዎቹን ሁሉ ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠሩ።

ዘሌዋውያን 8:9

እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት፣ ሙሴ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ ላይ አደረገ፤ በመጠምጠሚያው ላይ በፊት ለፊቱ በኩል የተቀደሰውን የወርቅ አክሊል አደረገለት።

ዘኍል 7:14

ዐሥር ሰቅል የሚመዝን በዕጣን የተሞላ የወርቅ ጭልፋ፣

ዘኍል 31:50-51

ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የእግር ዐልቦዎች፣ የእጅ አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጕትቻዎችና የዐንገት ሐብሎች በእግዚአብሔር ፊት ማስተስረያ እንዲሆነን መባ አድርገን ለእግዚአብሔር አምጥተናል።”

ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በጌጣጌጥ መልክ የተሠራውን ወርቅ ሁሉ ተቀበሏቸው።

ዘዳግም 7:25

የአማልክታቸውን ምስሎች በእሳት አቃጥል፤ በላያቸው የሚገኘውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ ለራስህ አታድርግ፤ አለዚያ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ስለ ሆነ ያሰናክልሃል።

ዘዳግም 8:13

ደግሞም የከብት፣ የበግና የፍየል መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበረክት፣ ያለህም ሁሉ በላይ በላዩ እየጨመረ ሲሄድ፣

ዘዳግም 17:17

ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፤ ብዙ ብርና ወርቅም አያግበስብስ።

ኢያሱ 6:19

ብሩና ወርቁ እንዲሁም የናሱና የብረቱ ዕቃ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ስለ ሆነ፣ ወደ እግዚአብሔር ግምጃ ቤት ይግባ።”

ኢያሱ 7:21

ከምርኮው ዕቃ መካከል ከሰናዖር የመጣ አንድ የሚያምር ካባ፣ ሁለት መቶ ሰቅል ብርና ክብደቱ ዐምሳ ሰቅል የሚሆን የወርቅ ቡችላ አይቼ ጐመጀሁ፤ ወሰድኋቸውም፤ ዕቃውም ብሩ ከታች ሆኖ፣ በድንኳኔ ውስጥ መሬት ተቀብሯል።”

መሳፍንት 8:24-26

እርሱም፣ “አንድ የምጠይቃችሁ ነገር አለኝ፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁ ከምርኮ ካገኛችሁት ውስጥ የጆሮ ጕትቻችሁን እንድትሰጡኝ ነው” አላቸው፤ የወርቅ ጕትቻ ማድረግ የእስማኤላውያን ባህል ነበርና።

እነርሱም መልሰው፤ “ደስ እያለን እንሰጥሃለን” አሉት፤ ወዲያው ልብስ አነጠፉ፤ በላዩም ላይ እያንዳንዳቸው ከማረኩት ውስጥ የጆሮ ጕትቻ ጣል ጣል አደረጉለት።

ሌሎቹን ጌጣጌጦች፣ ይኸውም የዐንገት ሐብሉን ከነ እንጥልጥሉ፣ የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ ወይም በግመሎቻቸው ዐንገት ላይ ያሉትን ጌጦች ሳይጨምር ጌዴዎን በጠየቃቸው መሠረት የሰጡት የወርቅ ጕትቻ ክብደት ሺሕ ሰባት መቶ ሰቅል ያህል መዘነ።

1 ሳሙኤል 6:8

የእግዚአብሔርን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ በታቦቱም አጠገብ ባለው ሣጥን ውስጥ ለበደል መሥዋዕት የምትልኩትን የወርቅ ምስሎች አስቀምጡ፤ በፈለገውም መንገድ እንዲሄድ ልቀቁት፤

2 ሳሙኤል 8:7

ዳዊት የአድርአዛር ሹማምት ያነገቧቸውን የወርቅ ጋሻዎች ወስዶ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው።

1 ነገሥት 6:20-22

ቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ ከዝግባ የተሠራውንም መሠዊያ በወርቅ ለበጠው።

ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በወርቅ በተለበጠው ቅድስተ ቅዱሳን ፊት ለፊትም የወርቅ ሰንሰለቶች ዘረጋ።

ስለዚህ ውስጡን በሙሉ በወርቅ ለበጠው፤ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ያለውን መሠዊያም እንደዚሁ በወርቅ ለበጠው።

1 ነገሥት 6:30

እንዲሁም የቅድስተ ቅዱሳኑንና የመቅደሱን ወለል በሙሉ በወርቅ ለበጠ።

1 ነገሥት 7:48-50

እንደዚሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሠራ፤ እነዚህም፦ የወርቅ መሠዊያ፣ የገጸ ኅብስቱ ጠረጴዛ፣

በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ዐምስቱ በቀኝ፣ ዐምስቱ በግራ የሚቀመጡ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞችን፣ ከወርቅ የተቀረጹ አበቦችን፣ ቀንዲሎችንና መኰስተሪያዎችን፤

በሮቹ በሙሉ ባለአራት ማእዘን መቃኖች ያሏቸው፣ በሦስት ምድብ የተከፈሉና ትይዩ ነበሩ።

ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ጽዋዎችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ጭልፋዎችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።

1 ነገሥት 9:28

እነዚያም ወደ ኦፊር ሄደው አራት መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ ይዘው ተመለሱ፤ ይህንም ወደ ንጉሥ ሰሎሞን አመጡ።

1 ነገሥት 10:2

ታላቅ አጀብ አስከትላ ሽቱ፣ እጅግ ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮችን በግመሎች አስጭና ኢየሩሳሌም ከደረሰች በኋላ፣ ወደ ሰሎሞን ገብታ በልቧ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት።

1 ነገሥት 10:10-11

ከዚያም ለንጉሡ አንድ መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ቅመማ ቅመሞችና የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰሎሞን ያበረከተችለትን ያን ያህል ብዛት ያለው ቅመማ ቅመም ከዚያ በኋላ ከቶ አልመጣም።

ከኦፊር ወርቅ ያመጡት የኪራም መርከቦች፣ እጅግ ብዙ የሰንደል ዕንጨትና የከበሩ ድንጋዮች አመጡ።

1 ነገሥት 10:14-18

ለሰሎሞን በየዓመቱ የሚገባለት ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት የሚመዝን ወርቅ ነበር።

ይህም ከታላላቅና ከተራ ነጋዴዎች ከሚገባው ቀረጥ፣ መላው የዐረብ ነገሥታት ከሚያስገቡትና አገረ ገዦች ከሚሰበስቡት ግብር ሌላ ነበር።

ንጉሥ ሰሎሞን ከጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ ትላልቅ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱም ጋሻ የገባው ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ነበር።

እንዲሁም ከጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት መቶ ትንንሽ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱ ጋሻ የገባው ጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት ምናን ነበር። ንጉሡም ጋሻዎቹን የሊባኖስ ደን በተባለው ቤተ መንግሥት ውስጥ አኖረ።

ከዚያም ንጉሡ በዝኆን ጥርስ ትልቅ ዙፋን ሠርቶ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

1 ነገሥት 10:21-22

ንጉሥ ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው ቤተ መንግሥት ውስጥ የነበሩትም ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ በሰሎሞን ዘመን ብር ዋጋ እንደሌለው ስለሚቈጠር ከብር የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም።

ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋራ ዐብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ የንግድ መርከቦች ነበሩት። እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ያመጡ ነበር።

1 ነገሥት 12:28

ንጉሡ ከመከረበት በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጆች አሠርቶ ሕዝቡን፣ “እስራኤል ሆይ፤ ወደ ኢየሩሳሌም እስካሁን የወጣኸው ይበቃል፤ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነዚህ ናቸው” አለ።

1 ዜና መዋዕል 29:2-7

እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን፣ ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናሱ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ሥራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሚሆነውን መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን የከበሩ ድንጋዮች፣ ማንኛውንም ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።

ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን ወድሱት” አላቸው። ስለዚህ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ወደሱ፤ በእግዚአብሔር በንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ።

በማግስቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠዉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም አቀረቡ፤ ይህም አንድ ሺሕ ወይፈን፣ አንድ ሺሕ አውራ በግ፣ አንድ ሺሕ የበግ ጠቦት ሲሆን፣ ከመጠጥ ቍርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዋዕቶች ጋራ ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ።

በዚያችም ዕለት በእግዚአብሔር ፊት በታላቅ ደስታ በሉ፤ ጠጡም። ከዚያም የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ መሆኑን ለሁለተኛ ጊዜ በይፋ ዐወቁ፤ ገዥ እንዲሆንም በእግዚአብሔር ፊት ቀቡት፤ ሳዶቅንም ካህናቸው እንዲሆን ቀቡት።

ሰሎሞንም ነግሦ በአባቱ በዳዊት ምትክ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ ተከናወነለት፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።

የጦር አለቆቹና ኀያላኑ ሁሉ እንዲሁም የንጉሡ የዳዊት ወንዶች ልጆች በሙሉ ታማኝነታቸውን ለንጉሥ ሰሎሞን አረጋገጡለት።

እግዚአብሔርም ሰሎሞንን በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ሁሉ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከርሱ በፊት ለነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ያላጐናጸፋቸውን ንጉሣዊ ክብር ሁሉ ሰጠው።

የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር።

እርሱም በኬብሮን ሰባት ዓመት፣ በኢየሩሳሌም ሠላሳ ሦስት ዓመት፣ በአጠቃላይ አርባ ዓመት ነገሠ።

ብዙ ዘመን ባለጠግነትና ክብር ሳይጐድልበት ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ልጁ ሰሎሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ድርጊት በባለራእዩ በሳሙኤል የታሪክ መጽሐፍ፣ በነቢዩ በናታን የታሪክ መጽሐፍ፣ በባለራእዩ በጋድ የታሪክ መጽሐፍ ተጽፏል።

ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤

የተጻፈውም በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ ከፈጸማቸው ዝርዝር ጕዳዮችና በዙሪያው ከከበቡት፣ ከእስራኤልና ከሌሎች አገር መንግሥታት ታሪክ ጋራ ነው።

ይህም ሦስት ሺሕ መክሊት የኦፊር ወርቅና ሰባት ሺሕ መክሊት ንጹሕ ብር ለቤተ መቅደሱ የግድግዳ ግንብ ማስጌጫ

እንዲሁም ለወርቁ ሥራ፣ ለብሩ ሥራ፣ በየእጅ ጥበብ ባለሙያ ለሚሠራው ሥራ ሁሉ የሚሆን ነው። ታዲያ ዛሬ ራሱን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ፈቃደኛ የሚሆን ማን ነው?”

ከዚያም የቤተ ሰብ መሪዎች፣ የነገዱ የእስራኤል ሹማምት፣ የሻለቆችና የመቶ አለቆች እንዲሁም በንጉሡ ሥራ ላይ የተመደቡ ሹማምት በፈቃዳቸው ሰጡ፤

ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሰጡትም ዐምስት ሺሕ መክሊት ወርቅ፣ ዐሥር ሺሕ ዳሪክ ወርቅ፣ ዐሥር ሺሕ መክሊት ብር፣ ዐሥራ ስምንት ሺሕ መክሊት ናስ አንድ መቶ ሺሕ መክሊት ብረት ነው።

2 ዜና መዋዕል 1:15

ንጉሡ በኢየሩሳሌም ብሩንና ወርቁን እንደ ማንኛውም ድንጋይ፣ የዝግባውንም ዕንጨት ብዛት በየኰረብታው ግርጌ እንደሚበቅል ሾላ አደረገው።

2 ዜና መዋዕል 3:4-6

በቤተ መቅደሱ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ርዝመቱ በቤተ መቅደሱ ወርድ ልክ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ከፍታውም ሃያ ክንድ ነበር። ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

የቤተ መቅደሱን ዋና ክፍል በጥድ ዕንጨት አልብሶ በተጣራ ወርቅ ለበጠው፤ የዘንባባና የሰንሰለት አምሳልም ቀረጸበት።

ቤተ መቅደሱን በከበረ ድንጋይ አስጌጠው፤ የተጠቀመበትም ወርቅ የፈርዋይም ወርቅ ነበር።

2 ዜና መዋዕል 4:20-22

በተሰጠው መመሪያ መሠረት፣ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት እንዲነድዱ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞች ከነቀንዲሎቻቸው፣

ከወርቅ የተቀረጹ አበባዎችን እና ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መኰስተሪያዎችን፤

ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት መኰስተሪያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅደሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።

2 ዜና መዋዕል 9:9

ከዚያም ለንጉሡ አንድ መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ቅመማ ቅመሞችና የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰሎሞን እንደ ሰጠችው ዐይነት ቅመማ ቅመም ያለ ከቶ አልነበረም።

2 ዜና መዋዕል 9:13-17

ለሰሎሞን በየዓመቱ የሚገባለት ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት መክሊት የሚመዝን ወርቅ ነበር።

ይህም ከታላላቅና ከተራ ነጋዴዎች ከሚገባው ቀረጥ ሌላ ነበር። መላው የዐረብ ነገሥታትና አገረ ገዦች ለሰሎሞን ወርቅና ብር ያመጡለት ነበር።

ንጉሥ ሰሎሞን ሁለት መቶ ከጥፍጥፍ ወርቅ ትላልቅ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱም ጋሻ የገባው ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ነበር።

እንዲሁም ከጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት መቶ ትንንሽ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእነዚህም በእያንዳንዱ ጋሻ የገባው ጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበር። ንጉሡም ጋሻዎቹን “የሊባኖስ ደን” በተባለው ቤተ መንግሥት ውስጥ አኖረ።

ከዚያም ንጉሡ በዝኆን ጥርስ ትልቅ ዙፋን ሠርቶ በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

2 ዜና መዋዕል 24:14

ከጨረሱም በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ወደ ዮዳሄ አመጡ፤ በገንዘቡም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ዕቃዎች ማለትም ለአገልግሎትና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚውሉ ዕቃዎች እንደዚሁም ጭልፋዎችና ሌሎች የወርቅና የብር ዕቃዎችም ተሠሩ። ዮዳሄ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚቃጠል መሥዋዕት ዘወትር ይቀርብ ነበር።

ዕዝራ 1:4

ባሉበት ስፍራ የሚቀሩ በየትኛውም አገር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ስጦታ እንዲሆን ከበጎ ፈቃድ ስጦታ በተጨማሪ ብርና ወርቅ፣ ዕቃና እንስሳ በመስጠት ይርዷቸው።’ ”

ዕዝራ 8:25-27

ንጉሡ፣ አማካሪዎቹ፣ ሹሞቹና በዚያ የነበሩ እስራኤል ሁሉ ለአምላካችን ቤት የሰጡትን ብር፣ ወርቅና ዕቃ ሁሉ መዝኜ ሰጠኋቸው።

ስድስት መቶ ዐምሳ መክሊት ብር፣ አንድ መቶ መክሊት የብር ዕቃዎች፣ አንድ መቶ መክሊት ወርቅ፣

አንድ ሺሕ ዳሪክ የሚያወጡ ሃያ የወርቅ ወጭቶችና እንደ ወርቅ ነጥረው ከሚያብረቀርቅ ናስ የተሠሩ ሁለት ዕቃዎችን መዝኜ በእጃቸው አስረከብኋቸው።

ነህምያ 7:70-71

አንዳንድ የየቤተ ሰቡ አባቶች ለሥራው መዋጮ አደረጉ፤ አገረ ገዥውም 1,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 50 ድስቶች፣ 530 አልባሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጠ።

ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 ምናን ብር ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።

አስቴር 1:6

አደባባዩም ከነጭና ከሰማያዊ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ነበሩት፤ እነርሱም የብር ቀለበት በተበጀላቸው፣ ከነጭ በፍታና ከሐምራዊ ቀለም በተሠሩ ገመዶች በዕብነ በረዱ ምሰሶዎች ላይ ተንጠልጥለው ነበር። ነጭና ቀይ ቀለማት ተሰበጣጥረው በተነጠፉበት ወለል ላይ የወርቅና የብር ድንክ ዐልጋዎች ነበሩ፤ እነርሱም ከዕብነ በረድ፣ ቀስተ ደመና ከሚመስሉ ቀለሞችና ከሌሎች የከበሩ ድንጋዮች የተሠሩ ነበሩ።

ኢዮብ 22:24-25

የወርቅህን አንኳር ትቢያ ላይ፣ የኦፊር ወርቅህንም ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ ብትጥለው፣

ሁሉን ቻዩ አምላክ ወርቅ ይሆንልሃል፤ ምርጥ ብር ይሆንልሃል።

ኢዮብ 28:15-19

ንጹሕ ወርቅ ሊገዛት አይችልም፤ ዋጋዋም በብር አይመዘንም።

በኦፊር ወርቅ፣ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።

ወርቅም ብርሌም አይወዳደሯትም፤ በወርቅ ጌጥም አትለወጥም።

ዛጐልና አልማዝ ከቍጥር አይገቡም፤ የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍም ይበልጣል።

የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን ሊስተካከላት አይችልም፤ ዋጋዋም በንጹሕ ወርቅ አይተመንም።

መዝሙር 45:9

ከተከበሩት ሴቶችህ መካከል የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በኦፊር ወርቅ አጊጣ በቀኝህ ቆማለች።

መዝሙር 68:13

በበጎች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ፣ ከብር እንደ ተሠሩ የርግብ ክንፎች፣ በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ።”

ምሳሌ 3:14-15

እርሷ ከብር ይልቅ ትርፍ የምታመጣ፣ ከወርቅም ይልቅ ጥቅም የምታስገኝ ናትና።

ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤ አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።

ምሳሌ 8:10

ከብር ይልቅ ምክሬን፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ፤

ምሳሌ 8:19

ፍሬዬ ከንጹሕ ወርቅ ይበልጣል፤ ስጦታዬም ከነጠረ ብር።

ምሳሌ 16:16

ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት፣ ከብርም ማስተዋልን መምረጥ ምንኛ ይበልጣል!

ምሳሌ 25:12

የጠቢብ ሰው ዘለፋ ለሚሰማ ጆሮ፣ እንደ ወርቅ ጕትቻ ወይም እንደ ጥሩ የወርቅ ጌጥ ነው።

መክብብ 2:8

ለራሴም ብርንና ወርቅን፣ የነገሥታትና የአውራጃዎችን ሀብት አካበትሁ፤ ወንድና ሴት አዝማሪዎች፣ የሰው መደሰቻ የሆኑ ቅምጦች ነበሩኝ።

ማሕልየ መሓልይ 1:11

እኛም ባለብር ፈርጥ፣ የወርቅ ጕትቻ እናሠራልሻለን።

ኢሳይያስ 2:7

ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ሀብታቸውም ልክ የለውም። ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤ የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም።

ኢሳይያስ 2:20

በዚያ ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።

ኢሳይያስ 60:9

በርግጥ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ እርሱ ክብሩን ስላጐናጸፈሽ፣ ለእስራኤል ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር አምላክሽ ክብር፣ ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን፣ ከነብራቸውና ከነወርቃቸው ለማምጣት፣ የተርሴስ መርከቦች ቀድመው ይወጣሉ።

ኢሳይያስ 60:17

በናስ ፈንታ ወርቅ፣ በብረትም ፈንታ ብር አመጣልሻለሁ። በዕንጨት ፈንታ ናስ በብረትም ፈንታ ድንጋይ አመጣልሻለሁ። ሰላምን ገዥሽ፣ ጽድቅንም አለቃሽ አደርጋለሁ።

ኤርምያስ 10:9

የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣ ወርቅም ከአፌዝ ይመጣል። የእጅ ጥበብ ባለሙያና አንጥረኛው የሠሯቸው፣ ብልኀተኞችም ያበጇቸው ሁሉ፣ ሰማያዊና ሐምራዊ ልብስ ተጐናጽፈዋል።

ኤርምያስ 51:7

ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ ምድርንም ሁሉ አሰከረች። ሕዝቦች ከወይን ጠጇ ጠጡ፤ ስለዚህ አሁን አብደዋል።

ሰቈቃወ 4:1-2

ወርቁ እንዴት ደበሰ! ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ! የከበሩ ድንጋዮች፣ በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል።

ሕዝቤ ባለቀበት ጊዜ፣ ምግብ እንዲሆኗቸው፣ ርኅሩኆቹ ሴቶች በገዛ እጆቻቸው፣ ልጆቻቸውን ቀቀሉ።

እግዚአብሔር ለመቅሠፍቱ መውጫ በር ከፈተ፤ ጽኑ ቍጣውን አፈሰሰ፤ መሠረቷን እንዲበላ፣ በጽዮን እሳት ለኰሰ።

ጠላቶችም ሆኑ ወራሪዎች፣ የኢየሩሳሌምን በሮች ጥሰው ይገባሉ ብለው፣ የምድር ነገሥታት፣ ወይም ከዓለም ሕዝብ አንዳቸውም አላመኑም።

ይህ ግን ከነቢያት ኀጢአት፣ ከካህናቷም መተላለፍ የተነሣ ሆኗል፤ በውስጧ፣ የጻድቃንን ደም አፍስሰዋልና።

እንደ ታወሩ ሰዎች፣ በየመንገዱ ላይ ይደናበራሉ፤ ማንም ሰው ደፍሮ ልብሳቸውን መንካት እስከማይችል ድረስ፣ በደም እጅግ ረክሰዋል።

ሰዎች “ሂዱ! እናንተ ርኩሳን!” ብለው ይጮኹባቸዋል፤ “ወግዱ! ወግዱ! አትንኩ!” ይሏቸዋል፤ ሸሽተው በሚቅበዘበዙበትም ጊዜ፣ በአሕዛብ መካከል ያሉ ሰዎች፣ “ከእንግዲህ በዚህ መቀመጥ አይገባቸውም!” ይላሉ።

እግዚአብሔር ራሱ በትኗቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ አይጠብቃቸውም፤ ካህናቱ አልተከበሩም፤ ሽማግሌዎቹም ከበሬታ አላገኙም።

ከሁሉም በላይ በከንቱ ርዳታን ስንጠባበቅ፣ ዐይኖቻችን ደከሙ፤ ከግንብ ማማችን ላይ ሆነን፣ ሊያድን ከማይችል ሕዝብ ርዳታ ጠበቅን።

ሰዎች እግር እግራችንን ተከታተሉን፤ ስለዚህ በመንገዳችን መሄድ አልቻልንም፤ መጨረሻችን ቀርቧል፤ ቀኖቻችንም ተቈጥረዋል፤ ፍጻሜያችን መጥቷልና።

ከሰማይ ንስሮች ይልቅ፣ ጠላቶቻችን ፈጣኖች ናቸው፤ በተራሮች ላይ አሳደዱን፤ በምድረ በዳም ሸመቁብን።

እንደ ወርቅ ይቈጠሩ የነበሩ፣ የከበሩ የጽዮን ወንዶች ልጆች፣ የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው፣ እንዴት አሁን እንደ ሸክላ ዕቃ ሆኑ!

ሕዝቅኤል 7:19

“ ‘ብራቸውን በየጐዳናው ይጥላሉ፤ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቈጠራል። በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ በኀጢአት እንዲወድቁ ዕንቅፋት ሆኖባቸዋልና በልተው አይጠግቡበትም፤ ሆዳቸውንም አይሞሉበትም።

ሕዝቅኤል 16:13

በወርቅና በብር አጌጥሽ፤ ልብስሽም ያማረ በፍታ፣ ሐርና ወርቀ ዘቦ ነበር፤ ምግብሽም የላመ ዱቄት፣ ማርና የወይራ ዘይት ነበር። እጅግ ውብ ሆንሽ፤ ንግሥት ለመሆንም በቃሽ።

ሕዝቅኤል 16:17

ከሰጠሁሽ ወርቄና ብሬ የተሠራውን ምርጥ ጌጣጌጥ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ አበጀሽ፤ ከእነርሱም ጋራ ዝሙት ፈጸምሽ።

ዳንኤል 3:1

ንጉሡ ናቡከደነፆር ከፍታው ስድሳ ክንድ፣ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው።

ሆሴዕ 2:8

እርሷም እህል፣ ዘይትና አዲስ የወይን ጠጅ የሰጠኋት፣ ለበኣል አምልኮ ያደረጉትን፣ ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት፣ እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም።

ኢዩኤል 3:5

ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፤ የተመረጠውንም ንብረቴን ተሸክማችሁ ወደ ቤተ መቅደሳችሁ አስገብታችኋልና።

አሞጽ 8:6

ድኻውን በብር፣ ችግረኛውንም በጥንድ ጫማ እንገዛለን፤ ግርዱን እንኳ በስንዴ ዋጋ እንሸጣለን።

ናሆም 2:9

ብሩን ዝረፉ! ወርቁን ንጠቁ! በየግምጃ ቤቱ ያለው፣ የተከማቸውም ሀብት ስፍር ቍጥር የለውም።

ዘካርያስ 13:9

ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤ እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤ እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ፤ እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”

ሚልክያስ 3:3

ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ ሌዋውያንንም አንጽቶ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል፤ ከዚያም እግዚአብሔር ቍርባንን በጽድቅ የሚያቀርቡ ሰዎች ይኖሩታል፤

ማቴዎስ 2:11

ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩ፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት።

ማቴዎስ 6:19-21

“ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በሚችልበት በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ።

“ግብዞች በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በየጐዳናውና በየምኵራቡ እንደሚያደርጉት፣ አንተም ለድኾች ምጽዋት በምትሰጥበት ጊዜ ይታይልኝ ብለህ ጥሩንባ አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል።

ነገር ግን ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በማይችልበት በዚያ በሰማይ ለራሳችሁ ሀብት አከማቹ፤

ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና።

ማቴዎስ 23:16-17

“እናንተ ዕውር መሪዎች፤ ወዮላችሁ! ‘ማንም በቤተ መቅደስ ቢምል ምንም አይደለም፤ ነገር ግን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል መሐላው ይደርስበታል’ ትላላችሁ።

እናንተ የታወራችሁ ተላላዎች! ከወርቁና ወርቁን ከቀደሰው ቤተ መቅደስ የቱ ይበልጣል?

ማቴዎስ 23:19

እናንተ ዕውሮች፤ ከመባውና መባውን ከቀደሰው መሠዊያ የቱ ይበልጣል?

ሐዋርያት ሥራ 3:6

ጴጥሮስ ግን፣ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ነገር ግን ያለኝን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ በእግርህ ተመላለስ” አለው፤

ሐዋርያት ሥራ 17:29

“እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን፣ አምላክ በሰው ሙያና ጥበብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ ይመስላል ብለን ማሰብ አይገባንም።

1 ቆሮንቶስ 3:12

ማንም በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ወይም በብር፣ በከበረ ድንጋይ ወይም በዕንጨት፣ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣

1 ጢሞቴዎስ 2:9

እንዲሁም ሴቶች በጨዋነትና ራስን በመግዛት ተገቢ የሆነ ልብስ ይልበሱ እንጂ በሹሩባ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋቸው ውድ በሆኑ ልብሶች አይሽቀርቀሩ፤

2 ጢሞቴዎስ 2:20

በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ ሳይሆን፣ የዕንጨትና የሸክላ ዕቃም ይኖራል፤ ከእነዚህ አንዳንዶቹ ለከበረ፣ ሌሎቹም ለተራ አገልግሎት ይውላሉ።

ዕብራውያን 9:4

በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠው የኪዳኑ ታቦት ነበሩ፤ ይህም ታቦት መና ያለበትን የወርቅ መሶብ፣ የለመለመችውን የአሮንን በትርና ኪዳኑ የተጻፈበትን ጽላት ይዟል።

ዕብራውያን 9:11-12

ክርስቶስ አሁን ስላሉት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ በመጣ ጊዜ፣ በሰው እጅ ወዳልተሠራችው፣ ከዚህ ፍጥረት ወዳልሆነችው ታላቅና ፍጹም ድንኳን ገባ።

የገባውም የፍየልንና የጥጃዎችን ደም ይዞ አይደለም፤ ነገር ግን የዘላለም ቤዛነት ሊያስገኝ የራሱን ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገባ።

1 ጴጥሮስ 1:7

እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ የደረሱት፣ በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ፣ እውነተኛ መሆኑ እንዲረጋገጥና ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ክብርንና ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው።

1 ጴጥሮስ 1:18-19

ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከንቱ ከሆነ ሕይወት የተዋጃችሁት በሚጠፋ ነገር፣ በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤

ነገር ግን እናንተ የተዋጃችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም፣ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው።

1 ጴጥሮስ 3:3-4

ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን፣ ይኸውም፣ ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በማጌጥና በልብስ አይሁን፤

ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምን ጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን፤

ራእይ 1:12-13

እኔም የሚናገረኝን ድምፅ ለማየት ዞር አልሁ፤ ዞር ባልሁም ጊዜ ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ፤

በመቅረዞቹም መካከል “የሰው ልጅ የሚመስል” አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ የሚደርስ መጐናጸፊያ የለበሰ፣ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።

ራእይ 17:4

ሴቲቱም ሐምራዊና ቀይ ልብስ ተጐናጽፋ ነበር፤ ደግሞም በወርቅ፣ በከበሩ ድንጋዮችና በዕንቈችም አጊጣ ነበር፤ በእጇም የሚያስጸይፍ ነገርና የዝሙቷ ርኩሰት የሞላበትን የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር።

ራእይ 21:18-21

ቅጥሩ የተሠራው ከኢያሰጲድ ነበር፤ ከተማዪቱም እንደ መስተዋት ንጹሕ ከሆነ ወርቅ የተሠራች ነበረች።

የከተማዪቱ ቅጥር መሠረቶች በሁሉም ዐይነት የከበረ ድንጋይ ያጌጡ ነበር፤ የመጀመሪያው መሠረት ኢያሰጲድ፣ ሁለተኛው ሰንፔር፣ ሦስተኛው ኬልቄዶን፣ አራተኛው መረግድ፣

ቅድስቲቱ ከተማ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባሏ እንደ ተዋበች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።

ዐምስተኛው ሰርዶንክስ፣ ስድስተኛው ሰርድዮን፣ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፣ ስምንተኛው ቢረሌ፣ ዘጠነኛው ወራውሬ፣ ዐሥረኛው ክርስጵራስስ፣ ዐሥራ አንደኛው ያክንት፣ ዐሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ።

ዐሥራ ሁለቱም በሮች ዐሥራ ሁለት ዕንቍዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱም በር ከአንድ ዕንየተሠራ ነበረ። የከተማዪቱም አውራ መንገድ እንደ መስተዋት ብርሃን የሚያስተላልፍ ንጹሕ ወርቅ ነበረ።

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚኦ እግዚአብሔር፥ ዘላለማዊ አምላክ፥ ልዑል ጌታ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ አንተ እመጣለሁ። አንተ ብቻ ለከፍተኛ ምስጋናና ለአምልኮ ብቁ ነህ። ቅዱስ አባት፥ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም ብዬ አምኜ ወደ አንተ እቀርባለሁ። በዚህ ቅጽበት ሕይወቴን ሁሉ ለአንተ አስገዛለሁ። ከወርቅና ከብር ይልቅ አንተን እንዳፈልግህና እንድፈልግህ ብርታት ስጠኝ። መንፈስ ቅዱስ፥ በቃልህ እንድጸናና በሌላ ነገር እንዳልጨነቅ እርዳኝ። ቃል ኪዳንህን እንደ ውድ ሀብት አድርጌ እንድይዝ እርዳኝ። ብሩና ወርቁ የአንተ ነውና፤ የሚያስፈልገኝን ሁሉ እንደምትሰጠኝ አውቃለሁ። ጌታ ሆይ፥ በክፉ ትውልድ መካከል እንዴት እንደምኖር እንዳውቅ፥ ልቤን ንጹሕ አድርጌ ለመጠበቅ የሚያስችል ጥበብና ድፍረትን ስጠኝ። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እምነቴ እንደ ወርቅ ተፈትኖ ለክብር ይገኝ ዘንድ፥ ጽኑ እምነት እንዲኖረኝ እርዳኝ። ደስታም ሆነ መከራ ለእድገቴ አስፈላጊ መሆኑን እንድገነዘብ አድርገኝ። ትልቁ ዋስትናዬ አንተ ከእኔ ጋር መሆንህ ነው። ድልን ለማግኘት የሚያስችለኝን ጸጋ ስጠኝ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም። አሜን!