ዘካርያስ 13:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤ እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤ እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ፤ እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፥ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፥ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፥ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል። |
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ወንዞችም አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
ያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ፤ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ይልሃል። የዐመፅ እስራትን ከመካከልህ ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ማንጐራጐርንም ብትተው፥
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፥ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለበጎነት እመለከተዋለሁ።
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
አራጣንም በአራጣ ላይ ይቀበላሉ፤ ተንኰልን በተንኰል ላይ ይሠራሉ፤ “እኔንም ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ይኸውም የእስራኤል ቤት ደግሞ ከእኔ ርቀው እንዳይስቱ፥ በኀጢአታቸውም ሁሉ እንዳይረክሱ ነው፤ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከእናንተም ዘንድ ዐመፀኞችንና የበደሉኝን እለያለሁ፤ ከኖሩባትም ምድር አወጣቸዋለሁ፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
እንዲህም ይሆናል፤ የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ይድናሉ። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምሥራች የሚሰበክላቸው ይገኛሉ።
ወድጃቸዋለሁና የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፥ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፣ አደላድላቸዋለሁም፣ እመልሳቸዋለሁ፣ እኔም አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፥ እኔም እሰማቸዋለሁና እንዳልጣልኋቸው ይሆናሉ።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
ከእነዚያ ዘመናት በኋላ ለቤተ እስራኤል የምገባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በልባቸው አሳድራለሁ፤ በሕሊናቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል ይላል እግዚአብሔር።
አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።
ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።