Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞችና በውሃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚነድድ ታላቅ ኮከብ በወንዞች አንድ ሦስተኛና በውሃ ምንጮች ላይ ከሰማይ ወደቀ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞችና በውሃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ የወደቀውም በወንዞች ሢሶና በውሃ ምንጮች ላይ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሦስተኛውም መልአክ ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፥ በወንዞችና በውኃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ። የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 8:10
21 Referencias Cruzadas  

ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ውጭ ያለ​ውን የው​ኃ​ውን ምንጭ ይደ​ፍኑ ዘንድ ከአ​ለ​ቆ​ቹና ከኀ​ያ​ላኑ ጋር ተማ​ከረ፤ እነ​ር​ሱም ምክ​ሩን ወደዱ።


ውኃ​ው​ንም ከሕ​ይ​ወት ምን​ጮች በደ​ስታ ትቀ​ዳ​ላ​ችሁ።


“አንተ በን​ጋት የሚ​ወጣ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ሆይ፥ እን​ዴት ከሰ​ማይ ወደ​ቅህ! ወደ አሕ​ዛ​ብም መል​እ​ክ​ትን የላ​ክህ አንተ ሆይ፥ እን​ዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀ​ጠ​ቀ​ጥህ!


በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


“በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ ዐሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ሰይ​ጣ​ንን ከሰ​ማይ እንደ መብ​ረቅ ሲወ​ድቅ አየ​ሁት።


የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።


ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።


በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።


ሦስተኛውም ጽዋውን በወንዞችና በውሃ ምንጮች ውስጥ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ።


በለስም በብርቱ ነፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፤


ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።


አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁም ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።


የሰዎችንም ሲሶ እንዲገድሉ ለሰዓቱና ለቀኑ ለወሩም ለዓመቱም ተዘጋጅተው የነበሩ አራቱ መላእክት ተፈቱ።


ከአፋቸውም በወጡት በእሳቱና በጢሱ በዲኑም በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች የሰዎቹ ሲሶ ተገደለ።


ከይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ በኢ​ጣም ዓለት ወዳ​ለው ዋሻ ወር​ደው ሶም​ሶ​ንን፥ “ገዢ​ዎ​ቻ​ችን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እን​ደ​ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምን? ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ይህ ምን​ድን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ችሁ እን​ዲሁ አደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸው” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos