መዝሙር 92:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ውኆች ድምፅ የተነሣ የባሕር እንቅስቃሴዋ ድንቅ ነው። ድንቅስ በልዕልና የሚኖር እግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ፥ የአንተ ታላላቅ ሥራዎች ደስ ያሰኙኛል፤ አንተ ስላደረግኻቸውም ነገሮች በደስታ እዘምራለሁ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የያዕቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበላችሁ፤ በአሕዛብም አለቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመስግኑም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል በሉ።
እናንተም ዛሬ ታዝናላችሁ፤ እንደገናም አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ድል በመንሣቱ የሚጠብቀን፥ በየሀገሩም ሁሉ የዕውቀቱን መዓዛ በእኛ የሚገልጥ እግዚአብሔር ይመስገን።