መዝሙር 6:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጭንቀቴ ደክሜአለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ። ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤ መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞት የሚያስታውስህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል። |
በመቃብር የሚኖሩ አያመሰግኑህምና፤ ሙታንም የሚያመሰግኑህ አይደሉምና፤ በሲኦልም የሚኖሩ ይቅርታህን ተስፋ አያደርጉምና።
“እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዐይኖቻችሁ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባን ያፍስሱ።
ዔ። የሚያጽናናኝ፥ ነፍሴንም የሚመልሳት ከእኔ ርቆአልና ዐይኔ ውኃ ያፈስሳል። ጠላት በርትቶአልና ልጆች ጠፍተዋል።
ቤት። በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፤ ከሚያፈቅሩአት ሁሉ የሚያጽናናት የለም፤ ወዳጆችዋም ሁሉ ወነጀሉአት፤ ጠላቶችም ሆኑአት።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።
በስተኋላውም በእግሮቹ አጠገብ ቆማ አለቀሰች፤ እግሮቹንም በእንባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕርዋም እግሮቹን ታብሰውና ትስመው፥ ሽቱም ትቀባው ነበር።