Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 69 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለ​ቃ​ለ​መ​ታ​ሰ​ቢያ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 አቤቱ፥ እኔን ለማ​ዳን ተመ​ል​ከት፤ አቤቱ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ፍጠን።

2 ነፍ​ሴን የሚ​ሹ​አት ይፈሩ፥ ይጐ​ስ​ቍ​ሉም፥ ክፉ​ንም የሚ​መ​ክ​ሩ​ብኝ ወደ​ኋ​ላ​ቸው ይመ​ለሱ፥ ይፈ​ሩም።

3 እሰይ! እሰይ! የሚ​ሉኝ አፍ​ረው ወዲ​ያው ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ።

4 አቤቱ፥ የሚ​ሹህ ሁሉ በአ​ንተ ሐሤት ያድ​ርጉ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤ ሁል​ጊዜ ማዳ​ን​ህን የሚ​ወ​ድዱ፥ “ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።

5 እኔ ድሃና ምስ​ኪን ነኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይረ​ዳ​ኛል፤ ረዳቴ መጠ​ጊ​ያ​ዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ አም​ላኬ አት​ዘ​ግይ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos