Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ለኤ​ዶ​ታም የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 “በአ​ን​ደ​በቴ እን​ዳ​ል​ስት አፌን እጠ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ኃጥ​ኣን በፊቴ በተ​ቃ​ወ​ሙኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖ​ራ​ለሁ” አልሁ፤

2 ዝም አልሁ ራሴ​ንም አዋ​ረ​ድሁ፥ ለበጎ ነገ​ርም ዝም አልሁ፥ ቍስ​ሌም ታደ​ሰ​ብኝ።

3 ልቤም በው​ስጤ ሞቀ​ብኝ፤ ከመ​ና​ገ​ሬም የተ​ነሣ እሳት ነደደ፥ በአ​ን​ደ​በ​ቴም ተና​ገ​ርሁ፦

4 “አቤቱ፥ ፍጻ​ሜ​ዬን አስ​ታ​ው​ቀኝ” አልሁ፥ የዘ​መኔ ቍጥ​ሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘን​ድስ ለምን ወደ ኋላ እላ​ለሁ?

5 እነሆ፥ ዘመ​ኖቼን አስ​ረ​ጀ​ሃ​ቸው፤ አካ​ሌም በፊ​ትህ እንደ ኢም​ንት ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሉ ከንቱ ነው።

6 ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመ​ላ​ለ​ሳል፥ ነገር ግን በከ​ንቱ ይታ​ወ​ካሉ። ያከ​ማ​ቻሉ የሚ​ሰ​በ​ስ​ቡ​ለ​ት​ንም አያ​ው​ቁም።

7 አሁ​ንስ ተስ​ፋዬ ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን? ትዕ​ግ​ሥ​ቴም ከአ​ንተ ዘንድ ነው።

8 ከኀ​ጢ​አቴ ሁሉ አዳ​ን​ኸኝ፥ ለሰ​ነ​ፎ​ችም ስድብ አደ​ረ​ግ​ኸኝ።

9 ዝም አልሁ አፌ​ንም አል​ከ​ፈ​ት​ሁም። አንተ ፈጥ​ረ​ኸ​ኛ​ልና፤

10 መቅ​ሠ​ፍ​ት​ህን ከእኔ አርቅ፥ ከእ​ጅህ ብር​ታት የተ​ነሣ አል​ቄ​አ​ለ​ሁና።

11 በተ​ግ​ሣ​ጽህ ስለ ኀጢ​አቱ ሰውን ዘለ​ፍ​ኸው፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም እንደ ሸረ​ሪት አቀ​ለ​ጥ​ኻት፤ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ በከ​ንቱ ይታ​ወ​ካሉ።

12 አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥ ልመ​ና​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ልቅ​ሶ​ዬ​ንም አድ​ምጥ፥ ቸልም አት​በ​ለኝ፤ እኔ በም​ድር ላይ መጻ​ተኛ ነኝና፥ እንደ አባ​ቶ​ችም ሁሉ እን​ግዳ ነኝና።

13 ወደ​ማ​ል​መ​ለ​ስ​በት ሳል​ሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos