Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 39:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ቍጥር የሌ​ላት ክፋት አግ​ኝ​ታ​ኛ​ለ​ችና፤ ኀጢ​አ​ቶቼ ተገ​ና​ኙኝ፥ ማየ​ትም ተስ​ኖ​ኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴን አድምጥ፤ ልቅሶዬንም ቸል አትበል፤ በአንተ ፊት እኔ መጻተኛ ነኝና፤ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በተግሣጽህ ስለ ኃጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ የሚመኘውንም እንደ ብል ታጠፋበታለህ፥ በእውነት ሰው ሁሉ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤ እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤ እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 39:12
19 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ብዙ ቀን እን​ግዳ ሆኖ ተቀ​መጠ።


ያዕ​ቆ​ብም ለፈ​ር​ዖን አለው፥ “በእ​ን​ግ​ድ​ነት የኖ​ር​ሁት የሕ​ይ​ወቴ ዘመ​ንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕ​ይ​ወ​ቴም ዘመ​ኖች ጥቂ​ትም ክፉም ሆኑ​ብኝ፤ አባ​ቶች በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ት​ንም ዘመን አያ​ህ​ሉም።”


ምና​ል​ባት መከ​ራ​ዬን አይቶ ስለ ርግ​ማኑ በዚህ ቀን መል​ካም ይመ​ል​ስ​ል​ኛል” አላ​ቸው።


“ተመ​ል​ሰህ የሕ​ዝ​ቤን ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፥ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ እኔ እፈ​ው​ስ​ሃ​ለሁ፤ እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትወ​ጣ​ለህ።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ስደ​ተ​ኞች እንደ ነበሩ እኛ በፊ​ትህ ስደ​ተ​ኞ​ችና መጻ​ተ​ኞች ነን፤ ዘመ​ና​ች​ንም በም​ድር ላይ እንደ ጥላ ናት፤ አት​ጸ​ና​ምም።


እኔ እንደ አረጀ ረዋት፥ ብልም እን​ደ​ሚ​በ​ላው ልብስ ነኝ።


“አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ምስ​ክሬ በሰ​ማይ አለ፤ የሚ​ያ​ው​ቅ​ል​ኝም በአ​ር​ያም ነው።


ነፍሴ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች። አጥ​ን​ቶ​ቼም ሁሉ የተ​ቀ​ደሰ ስሙን።


ክብሬ ይነሣ፥ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ ይነሣ፤ እኔም ማልጄ እነ​ሣ​ለሁ።


አቤቱ፥ አንተ ተስ​ፋዬ ነህና፤ ልዑ​ልን መጠ​ጊ​ያህ አደ​ረ​ግህ።


“ምድ​ርም ለእኔ ናትና፥ እና​ን​ተም በእኔ ፊት እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች ናች​ሁና ምድ​ርን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ሽጡ።


እን​ግ​ዲህ ሁል​ጊዜ እመኑ፥ ጨክ​ኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላ​ች​ሁም እና​ንተ እን​ግ​ዶች እንደ ሆና​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ከሥ​ጋ​ች​ሁም ተለ​ይ​ታ​ችሁ ወደ ጌታ​ችን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።


እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።


እር​ሱም ሥጋ ለብሶ በዚህ ዓለም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ፥ በታ​ላቅ ጩኸ​ትና እንባ ከሞት ሊያ​ድ​ነው ወደ​ሚ​ች​ለው ጸሎ​ት​ንና ምል​ጃን አቀ​ረበ፤ ጽድ​ቁ​ንም ሰማው።


ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።


ወዳጆች ሆይ! ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos