Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ። ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤ መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በሞት የሚያስታውስህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በጭ​ን​ቀቴ ደክ​ሜ​አ​ለሁ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ አል​ጋ​ዬን አጥ​ባ​ለሁ፥ በዕ​ን​ባ​ዬም መኝ​ታ​ዬን አር​ሳ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 6:6
23 Referencias Cruzadas  

ከመጮኼ ብዛት የተነሣ ደከምኩ፤ ጒሮሮዬም ቈሰለ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።


ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።


ጌታ ሆይ! የልቤን ፍላጎት ሁሉ ታውቃለህ፤ የእኔም መቃተት ለአንተ ምሥጢር አይደለም።


ሕዝቤ ስለ ተፈጀ፥ ሕፃናት በከተማይቱ መንገዶች ላይ ስለሚዝለፈለፉ፥ ዐይኖቼ በለቅሶ ደከሙ፤ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ፤ ተስፋም ቈረጥሁ።


“ጠላት ድል ስላደረገ ልጆቻችን ብቸኞች ሆነዋል፤ የሚያበረታታን አጽናኝ ከእኛ ስለ ራቀ፥ እንባ እያፈሰስን እናለቅሳለን።


በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጒንጮችዋ ላይ ይወርዳል፤ ከአፍቃሪዎችዋ ሁሉ እርስዋን የሚያጽናና አንድ እንኳ የለም፤ ወዳጆችዋ የነበሩ ሁሉ ከድተዋታል፤ በጠላትነትም ተነሥተውባታል።


“አሁንም ልቤ በመረረ ሐዘንና ሮሮ የተሞላ ነው፤ በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።


ወዳጆቼ በንቀት ይመለከቱኛል፤ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር አለቅሳለሁ።


የድካም ወሮቹ ለእኔ ጥቅም የለሽ ሆኑ፤ የችግር ሌሊቶቹም ለእኔ የጭንቅ ሌሊት ሆኑብኝ።


ከኢየሱስ በስተኋላ በእግሮቹ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች እግሮቹን በእንባዋ ታርስና በጠጒርዋ ታብስ ነበር፤ እግሮቹን እየሳመች ሽቶ ትቀባቸው ነበር።


ስለዚህ ጉዳይ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብዬ እንድናገር አዘዘኝ። “ሕዝቤ እጅግ ቈስሎአል፤ በብርቱም ተጐድቶአል፤ ስለዚህ ዐይኖቼ ቀንና ሌሊት እንባ ያፈሳሉ፤ ባለማቋረጥም አለቅሳለሁ።


ሐዘኔ ከመብዛቱ የተነሣ ዐይኖቼ ደከሙ፤ እግዚአብሔር ሆይ! በየቀኑ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እጆቼንም ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤ እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤ እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።


“መኖር ሰልችቶኛል፤ የማሳልፈውን መራራ ሕይወት በግልጽ አሰማለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! ስማኝ፤ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ሆይ! እርዳኝ።


ዘለዓለማዊ ፍቅርህ በመቃብር፥ ታማኝነትህ በጥፋት ቦታ ይነገራልን?


ወደ ዝምታ ዓለም፥ ወደ መቃብር የወረዱ ሙታን እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑት አይችሉም።


ከሙታን ዓለም ሊያመሰግንህ የሚችል አንድ እንኳ የለም፤ ሙታንም ሊያመሰግኑህ አይችሉም፤ ወደ መቃብር የወረዱትም ታማኝነትህን ተስፋ አያደርጉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios