Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በት​ዕ​ግ​ሥት ደጅ ጠና​ሁት፥ እር​ሱም ተመ​ልሶ ሰማኝ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ሰማኝ።

2 ከጥ​ፋት ጕድ​ጓድ ከረ​ግ​ረግ ጭቃም አወ​ጣኝ፥ እግ​ሮ​ቼ​ንም በዓ​ለት ላይ አቆ​ማ​ቸው፥ አረ​ማ​መ​ዴ​ንም አጸና።

3 አዲስ ምስ​ጋ​ናን በአፌ ጨመረ፥ ይህም የአ​ም​ላ​ካ​ችን ምስ​ጋ​ናው ነው፤ ብዙ​ዎች አይ​ተው ይፍሩ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይታ​መኑ።

4 መታ​መ​ኛው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የሆነ፥ ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰ​ትም፥ ያል​ተ​መ​ለ​ከተ ሰው ብፁዕ ነው።

5 አቤቱ አም​ላኬ፥ ብዙ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አደ​ረ​ግህ፥ አሳ​ብ​ህ​ንም ምንም የሚ​መ​ስ​ለው የለም፤ አወ​ራሁ፥ ተና​ገ​ርሁ፥ ከቍ​ጥ​ርም በዛ።

6 መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።

7 በዚ​ያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመ​ጽ​ሐፍ ራስ ተጽ​ፎ​አል፤

8 አም​ላኬ ሆይ፥ ፈቃ​ድ​ህን ለማ​ድ​ረግ መከ​ርሁ፥ ሕግ​ህም በልቤ ውስጥ ነው።”

9 በታ​ላቅ ጉባኤ ጽድ​ቅ​ህን አወ​ራሁ፤ እነሆ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤ አቤቱ፥ አንተ ጽድ​ቄን ታው​ቃ​ለህ።

10 ቅን​ነ​ት​ህን በልቤ ውስጥ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም፥ ማዳ​ን​ህ​ንም ተና​ገ​ርሁ፤ ይቅ​ር​ታ​ህ​ንና ምሕ​ረ​ት​ህን ከታ​ላቅ ጉባኤ አል​ሰ​ወ​ር​ሁም።

11 አቤቱ አንተ ይቅ​ር​ታ​ህን ከእኔ አታ​ርቅ፤ ቸር​ነ​ት​ህና እው​ነ​ትህ ዘወ​ትር ያግ​ኙኝ።

12 ቍጥር የሌ​ላት ክፋት አግ​ኝ​ታ​ኛ​ለ​ችና፤ ኀጢ​አ​ቶቼ ተገ​ና​ኙኝ፥ ማየ​ትም ተስ​ኖ​ኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።

13 አቤቱ፥ ታድ​ነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።

14 ነፍ​ሴን ለማ​ጥ​ፋት የሚ​ወ​ድዱ ይፈሩ፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይጐ​ስ​ቍሉ፤ በእኔ ላይ ክፋ​ትን ለማ​ድ​ረግ የሚ​ወ​ድዱ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለሱ፥ ይፈ​ሩም።

15 እሰይ፥ እሰይ የሚ​ሉኝ እፍ​ረ​ታ​ቸ​ውን ወዲ​ያ​ውኑ ይከ​ፈሉ።

16 አቤቱ፥ የሚ​ፈ​ል​ጉህ ሁሉ በአ​ንተ ደስ ይበ​ላ​ቸው፥ ሐሤ​ት​ንም ያድ​ርጉ፤ ሁል​ጊዜ ማዳ​ን​ህን የሚ​ወዱ ዘወ​ትር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው ይበሉ።

17 እኔ ድሃና ምስ​ኪን ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ያስ​ብ​ል​ኛል፤ አንተ ረዳ​ቴና መድ​ኀ​ኒቴ ነህ፤ አም​ላኬ ሆይ፥ አት​ዘ​ግይ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos