መዝሙር 52:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍ በልቡ፦ እግዚአብሔር የለም ይላል። ረከሱ፥ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ? አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣ እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ የዳዊት ትምህርት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ብርቱ ሰው፥ በእግዚአብሔር ወገኖች ላይ ክፉ ነገር በማድረግ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ መሆኑን እያወቅህስ ስለምን ዘወትር ትመካለህ? |
ከጠላት ድምፅ፥ ከኀጢአተኛም ማሠቃየት የተነሣ፥ ዐመፃን በላዬ መልሰውብኛልና፥ ሊያጠፉኝም ተነሥተውብኛልና።
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውምና፤ የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ በእጁ ውስጥ ናቸውና፥ ረዣዥም ተራሮች የእርሱ ናቸውና።
ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ‘ይህ የእኔ ነው’ ቢል፥ ክርክራቸው በፈጣሪ ፊት ይቅረብ፤ በፈጣሪ ፊት የተፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ ይክፈል።
ጽድቅን የሚናገር በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በከንቱ ነገር ታምነዋል፤ የማይጠቅማቸውንም ተናግረዋል፤ ኀጢአትን ፀንሰዋል፤ በደልንም ወልደዋል።
ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ንግግራቸው ሽንገላ ነው፤ ለባልንጀራቸው ሰላምን ይናገራሉ፤ በልባቸው ግን ጥላቻን ይይዛሉ።
ሐሜተኞች፥ እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ተሳዳቢዎች፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክሕተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸውም የማይታዘዙ ናቸው።
ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፤ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥
በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንድ ሰው በኔሴራ አቅራቢያ በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶርያዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ነበረ።