Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 52:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ አስ​ተ​ዋይ እን​ዳለ ያይ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ የሰው ልጆ​ችን ተመ​ለ​ከተ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንተ ማታለልን ሥራዬ ብለህ የያዝህ፤ አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ፣ ጥፋትን ያውጠነጥናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ኤዶማዊው ዶይቅ መጥቶ ለሳኦል፦ ዳዊት ወደ አቢሜሌክ ቤት መጥቷል ብሎ በነገረው ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንተ ተንኰለኛ ጥፋትህን ታሤራለህ፤ አንደበትህ እንደ ተሳለ ምላጭ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 52:2
21 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ይ​ልን በትር ከጽ​ዮን ይል​ክ​ል​ሃል፤ በጠ​ላ​ቶ​ች​ህም መካ​ከል ትገ​ዛ​ለህ።


ረድ​ኤቴ ሰማ​ይና ምድ​ርን ከፈ​ጠረ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።


የጽ​ድ​ቁን መሥ​ዋ​ዕት፥ መባ​ው​ንም፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በወ​ደ​ድህ ጊዜ፥ ያን​ጊዜ በመ​ሠ​ዊ​ያህ ላይ ፍሪ​ዳ​ዎ​ችን ይሠ​ዋሉ።


ቍጣ​ቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ ጆሮ​ዋም እንደ ደነ​ቈረ እባብ፥


ገለ​ዓድ የእኔ ነው፥ ምና​ሴም የእኔ ነው፤ ኤፍ​ሬም የራሴ መጠ​ጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው፤


በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤ በአፋቸው ሰይፍ አለና። የጠቢባን ምላስ ግን የቈሰለውን ይፈውሳል።


ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር፤ አላገኙም፤


በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ከመ​ም​ህ​ራ​ኑና ጠር​ጠ​ሉስ ከሚ​ባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በአ​ገረ ገዢው ዘንድ ከሰ​ሱት።


ይህን ሰው ሲሳ​ደ​ብና ወን​ጀል ሲሠራ፥ አይ​ሁ​ድ​ንም ሁሉ በየ​ሀ​ገሩ ሲያ​ውክ፥ ናዝ​ራ​ው​ያን የተ​ባ​ሉት ወገ​ኖች የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ት​ንም ክህ​ደት ሲያ​ስ​ተ​ምር አግ​ኝ​ተ​ነ​ዋል።


የሚ​ተ​ነ​ኰሉ፥ ራሳ​ቸ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሐዋ​ር​ያት የሚ​ያ​ስ​መ​ስሉ፥ ዐመ​ፅ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሐሰ​ተ​ኞች ሐዋ​ር​ያት አሉና።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።


ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳንና ኀይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።


የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ መልሶ፥ “የእ​ሴይ ልጅ ወደ ኖብ ወደ አኪ​ጦብ ልጅ ወደ ካህኑ አቤ​ሜ​ሌክ ሲመጣ አይቼ​ዋ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos