መዝሙር 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንጀታቸውን ቋጠሩ፥ አፋቸውም ትዕቢትን ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሲኦል አትተወኝምና፤ በአንተ የታመነውም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ታማኝህንም መበስበስ እንዲደርስበት አታደርግም። |
“ሲኦልም በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የአሕዛብን ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ያስነሡ፥ ምድርን የገዙአት አርበኞች ሁሉ በአንድነት በአንተ ላይ ተነሡ።
ሲኦልም ሆድዋን አስፍታለች፤ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች ባለጠጎቻቸውና ድሆቻቸውም ወደ እርስዋ ይወርዳሉ።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
“የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ያለጊዜአችን ልታጠፋን መጣህን? የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ፥ አንተ ማን እንደሆንህ ዐውቅሃለሁ” አለ።
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።