Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የአ​ሳፍ መዝ​ሙር።

1 የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፥ ምድ​ር​ንም ጠራት፤ ከፀ​ሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግ​ቢ​ያዋ ድረስ።

2 ከክ​ብሩ ውበት ከጽ​ዮ​ንም፥

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ልጥ ይመ​ጣል። አም​ላ​ካ​ች​ንም ዝም አይ​ልም፤ እሳት በፊቱ ይነ​ድ​ዳል፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ብዙ ዐውሎ አለ።

4 በላይ ያለ​ውን ሰማ​ይን ምድ​ር​ንም በሕ​ዝቡ ለመ​ፍ​ረድ ይጠ​ራል፥

5 እንደ ሕጉ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ ጻድ​ቃ​ኑን ሰብ​ስ​ቡ​ለት።

6 ሰማ​ያት ጽድ​ቁን ይና​ገ​ራሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና።

7 ሕዝቤ፥ ስማኝ ልን​ገ​ርህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እመ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ፤ አም​ላ​ክስ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝ።

8 ስለ መሥ​ዋ​ዕ​ትህ የም​ዘ​ል​ፍህ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባ​ን​ህም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነው።

9 ከቤ​ትህ ፍሪ​ዳን፥ ከመ​ን​ጋ​ህም ጊደ​ርን አል​ወ​ስ​ድም፤

10 የዱር አራ​ዊት ሁሉ፥ የም​ድረ በዳ እን​ስ​ሶ​ችና ላሞች ሁሉ የእኔ ናቸ​ውና።

11 የሰ​ማ​ይን አዕ​ዋፍ ሁሉ አው​ቃ​ለሁ፥ የዱር ውበ​ትም በእኔ ዘንድ አለ።

12 ብራ​ብም አል​ለ​ም​ን​ህም፥ ዓለም ሁሉ በመ​ላው የእኔ ነውና።

13 የፍ​ሪ​ዳ​ውን ሥጋ አል​በ​ላም፥ የፍ​የ​ሉ​ንም ደም አል​ጠ​ጣም።

14 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ጋ​ናን መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ፥ ለል​ዑ​ልም ጸሎ​ት​ህን ስጥ፤

15 በመ​ከ​ራህ ቀን ትጠ​ራ​ኛ​ለህ አድ​ን​ህ​ማ​ለሁ፥ አን​ተም ታከ​ብ​ረ​ኛ​ለህ።

16 ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለው፦ “ለምን አንተ ሕጌን ትና​ገ​ራ​ለህ? ኪዳ​ኔ​ንም በአ​ፍህ ለምን ትወ​ስ​ዳ​ለህ?

17 አን​ተስ ተግ​ሣ​ጼን ጠላህ፥ ቃሌ​ንም ወደ ኋላህ መለ​ስኽ።

18 ሌባ​ውን ባየህ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ትሮ​ጣ​ለህ፥ ዕድል ፋን​ታ​ህ​ንም ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር አደ​ረ​ግህ።

19 አፍህ ክፋ​ትን አበ​ዛች፥ አን​ደ​በ​ት​ህም ሽን​ገ​ላን ተበ​ተ​ባት።

20 ተቀ​ም​ጠህ ወን​ድ​ም​ህን ታማ​ዋ​ለህ፥ ለእ​ና​ት​ህም ልጅ ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖ​ርህ።

21 ይህን አድ​ር​ገህ ዝም አል​ሁህ፤ ኀጢ​አት አማ​ረ​ች​ህን? እኔ እን​ዳ​ንተ እሆን ዘንድ ጠረ​ጠ​ርህ? በፊ​ትህ ቆሜ ልዝ​ለ​ፍህ?

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ረሱ እና​ንተ፥ ይህን አስ​ተ​ውሉ፤ አለ​ዚያ ግን ይነ​ጥ​ቃል፥ የሚ​ያ​ድ​ንም የለም።

23 የከ​በ​ረች መሥ​ዋ​ዕት ታከ​ብ​ረ​ኛ​ለች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማዳ​ኑን ያሳ​የ​ባት መን​ገድ በዚያ አለች።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos