ሚክያስ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፥ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፥ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ተነሥተሽ አበራዪ፤ የብረት ቀንድ እሰጥሻለሁና፤ የናስ ሰኰና እሰጥሻለሁ፤ አሕዛብንም ታደቅቂአቸዋለሽ።” በግፍ ያግበሰበሱትን ትርፍ ለእግዚአብሔር፣ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትለዪአለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽዮን ልጅ ሆይ ተነሺ አሂጂ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ኮቴሽንም ናስ አደርጋለሁና፤ ብዙ ሕዝቦችን ታደቅቂአለሽ፤ እኔም ትርፋቸውን ለጌታ፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ አውለዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ሂዱና ጠላቶቻችሁን እንደ እህል አበራዩ! ቀንዱ ብረት፥ ሰኮናው ነሐስ እንደ ሆነ በሬ ብርቱ አደርጋችኋለሁ፤ ብዙ መንግሥታትን ትደመስሳላችሁ፤ እነርሱ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት ሁሉ ለመላው ዓለም ጌታ ለእኔ ለእግዚአብሔር አምጥታችሁ ታቀርባላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፥ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፥ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ። |
በዚያ ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከተዋረደና ከደከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለዓለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚያደርግና ከሚረገጥ፥ በሀገሩ ወንዝ ዳር ከሚኖር ሕዝብ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት በደብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀርባል።
እናንተ የተረፋችሁና መከራ የምትቀበሉ ሆይ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የነገረኝንና የሰማሁትን ስሙ።
ንግድዋና ዋጋዋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ንግድዋም በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ ለመብላትና ለመጠጣት፥ ለመጥገብም፥ በእግዚአብሔርም ፊት ለመታሰቢያ ይሆናል እንጂ ለእነርሱ አይሰበሰብም።
ፍላጾቻቸው ተስለዋል፤ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፤ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰረገሎቻቸውም መንኰራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈጠራል።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የባቢሎን ንጉሥ ቤት እንደ ተረገጠ አውድማ ናት፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።
ኤፍሬምም ቀንበርን እንደ ለመደች ጊደር ነው፤ እኔ ግን በአንገቱ ውበት እጫንበታለሁ፤ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፤ ይሁዳንም እለጕመዋለሁ፤ ያዕቆብም ለራሱ መንግሥትን ያስተካክላል።
የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።
በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፣ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፣ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ።
በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፣ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፣ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።
እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያንጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ ሰው ሁሉ በየሳምንቱ እሑድ የተቻለውን ያወጣጣ፤ ያገኘውንም በቤቱ ይጠብቅ።
ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ የናስና የብረትም ዕቃ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን፤ ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ።”