ኢሳይያስ 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 በዚያ ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከተዋረደና ከደከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለዓለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚያደርግና ከሚረገጥ፥ በሀገሩ ወንዝ ዳር ከሚኖር ሕዝብ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት በደብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀርባል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 በዚያ ጊዜ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፣ ረዣዥምና ቈዳው ከለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ከሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ከማይገባ፣ ወንዞችም ምድሩን ከሚከፍሉት መንግሥት፣ ገጸ በረከት ይመጣለታል፤ ገጸ በረከቱም የሚመጣለት የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 በዚያን ጊዜ ለሠራዊት ጌታ፥ ከረጅምና ከለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ከሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ከሆነና ከሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ከሚከፍሉት ሕዝብ ዘንድ ስጦታ ይመጣለታል፤ ስጦታውም የሠራዊት ጌታ ስም ወደሚገኝበት ወደ ጽዮን ተራራ ይቀርባል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የሠራዊት አምላክ በዓለም ሁሉ የመፈራት ግርማ ካላቸው፥ ቆዳቸው ለስላሳ፥ ቁመታቸው ረጅም ኀያላንና ብርቱዎች ከሆኑት፥ በወንዞች የተከፋፈለች ምድር ካላቸው ከእነዚያ ሕዝብ መባ የሚቀበልበት ጊዜ ይመጣል፤ እነርሱም የሠራዊት አምላክ ወደሚመለክባት ወደ ጽዮን ኰረብታ ይመጣሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 በዚያን ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከረጅምና ከለስላሳ ሕዝብ፥ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ከሆነ ወገን፥ ከሚሰፍርና ከሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ከሚከፍሉት ሕዝብ ዘንድ እጅ መንሻ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም ወደሚገኝበት ስፍራ ወደ ጽዮን ተራራ ይቀርባል። Ver Capítulo |