ዘካርያስ 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፣ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፣ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሷ ላይ በሚሰበሰቡበት በዚያ ቀን፣ ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ የማይነቃነቅ ዐለት አደርጋታለሁ፤ ለማነቃነቅ የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን ይጐዳሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ሊያጠቋት ቢሰበሰቡም፥ ሊያነሷት የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን እጅግ ይጎዳሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 በዚያን ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ እንደ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ እርስዋን ለማንሣት የሚሞክር ሁሉ ራሱን ይጐዳል፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እርስዋን ለማጥቃት ተባብረው ይመጣሉ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፥ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ። Ver Capítulo |