የእግዚአብሔርም ብርሃን በጥዋት፥ በማለዳም ፀሐይ ይወጣል፤ ብርሃኑም በነግህ ይመጣል፤ ከዝናምም የተነሣ በምድር ሐመልማል ይለመልማል።
ሚልክያስ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሓይ በክንፎቿ ፈውስ ይዛ ትወጣለች፤ እናንተም እንደ ሠባ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ ከጋጣ እንደ ወጡ ጥጃዎች ትቦርቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእናንተ ስሜን ለምታከብሩ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላችኋል፤ ፈውስንም ይሰጣችኋል። ከጒረኖ እንደ ተለቀቀ ጥጃ ትቦርቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፥ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ። |
የእግዚአብሔርም ብርሃን በጥዋት፥ በማለዳም ፀሐይ ይወጣል፤ ብርሃኑም በነግህ ይመጣል፤ ከዝናምም የተነሣ በምድር ሐመልማል ይለመልማል።
እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ በመቅሠፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
በዚያን ጊዜ አንካሳዎች እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ፤ የዲዳዎችም ምላስ ርቱዕ ይሆናል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በተጠማ መሬትም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
እርሱም፥ “የያዕቆብን ነገዶች እንደገና እንድታስነሣ፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ወደ አባቶች ቃል ኪዳን እንድትመልስ ባርያዬ ትሆን ዘንድ ለአንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኀኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ” ይላል።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤
እርሱ ግን ስለ ኀጢአታችን ቈሰለ፤ ስለ በደላችንም ታመመ፤ የሰላማችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
እኔ ከክፉ ቍስልሽ እፈውስሻለሁ፤ ጤናሽን እመልስልሻለሁ፤ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና።”
እነሆ ፈውስንና መድኀኒትን እሰጣታለሁ፤ እፈውሳታለሁም፤ የሰላምንና የእውነትንም መንገድ እገልጥላቸዋለሁ።
በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፤ ቅጠሉም አይረግፍም፤ ፍሬውም አይጐድልም፤ ውኃውም ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገኛል፤ ፍሬውም ለመብል፥ ቅጠሉም ለመድኀኒት ይሆናል።”
በመከራቸው ጊዜ በማለዳ ወደ እኔ ይገሰግሳሉ፤ እንዲህም ይላሉ፥ “ኑ፤ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናልና፥ እርሱም ይጠግነናል።
እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፣ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።
“በዐይናቸው አይተው፥ በልባቸውም አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው ዐይኖቻቸው ታወሩ፤ ልባቸውም ደነደነ።”
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።
“እናንተ ከአብርሃም ወገን የተወለዳችሁ ወንድሞቻችን እግዚአብሔርንም የምትፈሩ፥ ይህ የሕይወት ቃል ለእናንተ ተልኮአል።
እግዚአብሔር፦ እስከ ምድር ዳርቻ ላሉት ሁሉ መድኀኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ” ብሎ አዝዞናልና።
ይኸውም ዐይናቸውን ትከፍትላቸው ዘንድ፥ ከጨለማም ወደ ብርሃን፥ ሰይጣንን ከማምለክም ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ፥ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ፥ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋር አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው።’
ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤
ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
ዳግመኛ አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም ነገር በእርሱ በእናንተም እውነተኛ ነው፤ ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን ይበራል።
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”
እግዚአብሔር እንደ ሥራሽ ይስጥሽ፣ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት።