ዘሌዋውያን 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም የተልባ እግር ቀሚስና የተልባ እግር ሱሪ በሰውነቱ ላይ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ከበፍታ የተሠራ የውስጥ ሱሪውን ካጠለቀ በኋላ፣ የበፍታ ቀሚሱን ይልበስ፤ እሳቱ በመሠዊያው ላይ መሥዋዕቱን ከበላው በኋላ የሚቀረውን ዐመድ አንሥቶ፣ በመሠዊያው አጠገብ ያፍስስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ሰውነቱን ለመሸፈን የበፍታ ቀሚስና የበፍታ ሱሪ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ከከፈይ የተሠራ ቀሚሱንና ሱሪውን ለብሶ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳት ከበላው በኋላ የቀረውን ዐመድ ሰብስቦ በመሠዊያው ጐን ያፍስሰው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም የበፍታ ቀሚስና የበፍታ ሱሪ በሥጋው ላይ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል። |
ወደ ውጭውም አደባባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ፤ በተቀደሰውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑሩት፤ ሕዝቡንም በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላውን ልብስ ይልበሱ።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥቡታል። ካህኑም ሁሉን በመሠዊያው ላይ ለቍርባን ያቀርበዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
የተቀደሰውንም የተልባ እግር ቀሚስ ይልበስ፤ የተልባ እግርም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፤ የተልባ እግር መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የተልባ እግር አክሊልም በራሱ ላይ ያድርግ፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።
“ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የእህል ቍርባን ሁሉ እርሾ አይሁንበት፤ እርሾ ያለበት ነገር፥ ማርም ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ አታቀርቡምና።
ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደሚፈስስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስዱታል፤ በዕንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥሉታል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል።
ከካህናት ወገን ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤ በዘመናችሁ ለዘለዓለም ሕግ ነው። ከሚቃጠለው የእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።”
“አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዐቱንም ዘይት፥ ለኀጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ መሶብ ውሰድ፤