Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የሰማይም ሰራዊት ነጭ፣ ንጹሕና ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ ለብሰው፣ በነጫጭ ፈረሶች ላይ ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በሰማይም ያሉት ሠራዊት ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በነጭ ፈረሶች ላይ ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በነጫጭ ፈረሶች ላይ የተቀመጡ፥ ነጭና ንጹሕ የሆነ ውብ ልብስ የለበሱ የሰማይ ሠራዊት ተከትለውታል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 19:14
18 Referencias Cruzadas  

ከባ​ሪ​ያ​ህም ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና ፈጥ​ነህ ስማኝ።


መስ​ተ​ዋ​ቱ​ንም ከጥሩ በፍታ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ልብስ፥ ራስ ማሰ​ሪ​ያ​ው​ንም፥ ዐይነ ርግ​ቡ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል።


የተራሮችም ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳልና በተራሮች ሸለቆ ትሸሻላችሁ፣ በይሁዳም ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከሆነው ከምድር መናወጥ ፊት እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ፣ አምላኬ እግዚአብሔርም ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ይመጣል።


ወይስ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከዐሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይችል ይመስልሃልን?


መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።


ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ “እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኀጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል፤” ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።


አየሁም፤ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።


የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ።


እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል።” ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።


ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ በሰርዴስ ጥቂት ሰዎች ከአንተ ጋር አሉ፤ የተገባቸውም ስለ ሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።


በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤ በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።


ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos