Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 6:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ልብ​ሱ​ንም ያወ​ል​ቃል፤ ሌላም ልብስ ይለ​ብ​ሳል፤ አመ​ዱ​ንም ተሸ​ክሞ ከሰ​ፈሩ ንጹሕ ወደ ሆነ ስፍራ ወደ ውጭ ያወ​ጣ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚያም ልብሱን አውልቆ ሌላ ልብስ ይቀይር፤ ዐመዱንም ተሸክሞ ከሰፈር ውጭ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ ወደ ሆነ ስፍራ ይውሰድ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ልብሱንም ያወልቃል፥ ሌላም ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ተሸክሞ ከሰፈሩ ውጭ ወደ ሆነ ወደ ንጹሕ ስፍራ ያወጣዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚያም በኋላ ልብሱን ለውጦ ያን ዐመድ ተሸክሞ ከሰፈር ውጪ ያውጣ፤ ንጹሕ በሆነውም ቦታ ይድፋው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ልብሱንም ያወልቃል፥ ሌላም ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ተሸክሞ ከሰፈሩ ንጹሕ ስፍራ ወደ ሆነ ወደ ውጭ ያወጣዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 6:11
14 Referencias Cruzadas  

ሰባት ቀን መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


ወደ ውጭ​ውም አደ​ባ​ባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገ​ለ​ገ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያው​ልቁ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑ​ሩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ቀ​ድሱ ሌላ​ውን ልብስ ይል​በሱ።


ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።


ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ይሁን፤ በእ​ሳት ከተ​ደ​ረ​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ለእ​ርሱ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይብ​ሉት።”


ወይ​ፈ​ኑን ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደ​ሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ አመድ በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።


ወይ​ፈ​ኑ​ንም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም ወይ​ፈን እን​ዳ​ቃ​ጠሉ ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ የማ​ኅ​በሩ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


ካህ​ኑም የተ​ልባ እግር ቀሚ​ስና የተ​ልባ እግር ሱሪ በሰ​ው​ነቱ ላይ ይለ​ብ​ሳል፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት እሳቱ ከበ​ላው በኋላ አመ​ዱን አን​ሥቶ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ያፈ​ስ​ሰ​ዋል።


እሳ​ቱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ዘወ​ትር ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋም፤ ካህ​ኑም ማለዳ ማለዳ ዕን​ጨት ያቃ​ጥ​ል​በ​ታል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በዚያ ላይ ይረ​በ​ር​ባል፤ በዚ​ያም የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ስብ ያቃ​ጥ​ላል።


“እር​ሱን በቀ​ባ​ህ​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ መባ ይህ ነው። የኢፍ መስ​ፈ​ርያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካ​ሙን ዱቄት እኩ​ሌ​ታ​ውን በጥ​ዋት፥ እኩ​ሌ​ታ​ው​ንም በማታ ለዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባሉ።


ከል​ጆ​ቹም በእ​ርሱ ፋንታ የተ​ቀ​ባው ካህን ያቀ​ር​በ​ዋል። ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው፤ ሁል​ጊ​ዜም ይደ​ረ​ጋል።


ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በተ​ቀ​ደሰ ስፍ​ራም ይበ​ሉ​ታል፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos