ጠቦት ለማምጣት የሚበቃ ገንዘብ በእጅዋ ባይኖራት ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እርስዋም ትነጻለች።”
ዘሌዋውያን 4:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስቡ ሁሉ ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው የበግ ጠቦት ላይ እንደሚወሰድ ስብዋን ሁሉ ይወስዳሉ፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር በእሳት በተቃጠለው ቍርባን ላይ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥቡ ከኅብረት መሥዋዕት ጠቦት በወጣበት አኳኋን ሥቡን ሁሉ ያውጣ፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር በእሳት በሚቀርበው መሥዋዕት ላይ ያቃጥለው። በዚህ መሠረት ሰውየው የሠራውን ኀጢአት ካህኑ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው ጠቦት ላይ ስቡ እንደሚወሰድ እንዲሁ የእርሷን ስብ ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ለአንድነት መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን ስብ በመግፈፍ በሚፈጽመው ዐይነት የዚህችንም እንስሳ ስብ ሁሉ ገፎ ያስወግድ፤ እርሱንም ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው የምግብ መባ ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በዚህም ዐይነት ካህኑ ስለዚያ ሰው የኃጢአት መሥዋዕትን በማቅረብ ያስተስርይለት፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስቡ ሁሉ ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ጠቦት ላይ እንደሚወሰድ ስብዋን ይወስዳል፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር በእሳት በተቃጠለው ቍርባን ላይ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። |
ጠቦት ለማምጣት የሚበቃ ገንዘብ በእጅዋ ባይኖራት ሁለት ዋኖሶች፥ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፤ እርስዋም ትነጻለች።”
በካህኑም እጅ ውስጥ የቀረውን ዘይት ካህኑ በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያደርግበታል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል።
ካህኑም አንዲቱን ለኀጢአት መሥዋዕት፥ አንዲቱንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስተሰርይለታል።
ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት በእግዚአብሔር ፊት በበደል መሥዋዕት በግ ያስተሰርይለታል፤ የሠራውም ኀጢአት ይቀርለታል።
እንዲህም በወይፈኑ ያደርጋል፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕት በታረደው ወይፈን እንደ አደረገ እንዲሁ በዚህ ያደርጋል፤ ካህኑም ኀጢአታቸውን ያስተሰርያል፤ ኀጢአቸውም ይሰረይላቸዋል።
ስቡንም ሁሉ እንደ ደኅንነት መሥዋዕት ስብ፥ በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል። ካህኑም ኀጢአቱን ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
እንደ ሥርዐቱም ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል።
ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኀጢአት ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይቅር ይባልለታል። የተረፈውም እንደ እህሉ ቍርባን ለካህኑ ይሆናል።”
እግዚአብሔርን ስለ መበደሉና ስለ ሠራው ኀጢአት ከበጎቹ ነውር የሌለባትን እንስት በግ ወይም ከፍየሎች እንስት ፍየል ያመጣል፤ ካህኑም ስለ ኀጢአቱ ያስተሰርይለታል፤ ኀጢአቱም ይሰረይለታል።
ሙሴም አሮንን፥ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኀጢአትህን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፤ ለራስህና ለወገንህ አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቍርባን አቅርብ፤ አስተስርይላቸውም” አለው።
ካህኑም ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ያስተሰርይላቸዋል፤ ባለማወቅ ነበርና ይሰረይላቸዋል፤ እነርሱም ስለ ኀጢአታቸውና ስላለማወቃቸው ቍርባናቸውንና መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ።
ካህኑም ባለማወቅ ስለ በደለው ያስተሰርያል፤ ባለማወቅም በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ስለ ሠራው ሰው ያስተሰርይለታል።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
እንግዲህ ወደ ሰማያት የወጣ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን፤ በእርሱ በማመን ጸንተን እንኑር።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።
ነውር የሌለው ሆኖ፥ በዘለዓለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናመልከው ዘንድ ሕሊናችንን ከሞት ሥራ እንዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?
ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።