የሌዋዊውም የይምላእ ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያካፍል ሕዝቡ በፈቃዳቸው ለእግዚአብሔር በአቀረቡት ላይ ተሾመ።
ዘሌዋውያን 10:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን አላቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን የቀረውን የስንዴውን ቍርባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም አሮንንና የተረፉትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፤ “በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው የእህል ቍርባን የቀረውን ወስዳችሁ ቂጣ ጋግሩ፤ እጅግ ቅዱስ ስለ ሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትንም ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እጅግ የተቀደሰ ነውና ለጌታ ከሆነው በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የተረፈውን የእህሉን ቁርባን ውሰዱ፥ እርሾም ያልገባበት ቂጣ አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም አሮንንና ከሞት የተረፉትን ሁለቱን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታማርን እንዲህ አላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከቀረበው የምግብ መባ የተረፈውን ወስዳችሁ እርሾ ያልነካው ቂጣ ጋግሩ፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ መባ ስለ ሆነ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትንም ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን አላቸው፦ ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን የቀረውን የእህሉን ቍርባን ውሰዱ፥ ቂጣም አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት እግዚአብሔርም እንዲህ አዞኛልና፥ |
የሌዋዊውም የይምላእ ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያካፍል ሕዝቡ በፈቃዳቸው ለእግዚአብሔር በአቀረቡት ላይ ተሾመ።
ለመክበራቸው እጆቻቸውን ይቀድሱ ዘንድ በተቀደሱበት በዚያ ቦታ ይብሉት፤ የባዕድ ልጅ ግን አይብላው፤ የተቀደሰ ነውና።
አሮንም የአሚናዳብን ልጅ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ። እርስዋም ናዳብንና አብዩድን፥ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።
የእህሉን ቍርባንና የኀጢአትን መሥዋዕት የንስሓንም መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም ዘንድ እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።
እግዚአብሔርም እንዲህ አዝዞኛልና፥ ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን ለአንተም፥ ለልጆችህም የተሰጠ ሥርዐት ነውና በቅዱስ ስፍራ ትበሉታላችሁ።
ለአሮንና ለልጆቹም ይሁን፤ በእሳት ከተደረገው ከእግዚአብሔር ቍርባን ለዘለዓለም ሥርዐት ለእርሱ ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና በተቀደሰ ስፍራ ይብሉት።”